የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚዲያ ተቋማት የምስጋና ፕሮግራም አካሄድ
የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ነፃ የማስታወቂያ ሰዓት በመስጠት እንዲተዋወቅ እንዲሁም ማዕከሉ ድጋፍ እንዲያገኝ ስለአበረከቱትና እያበረከቱ ስላለው ድጋፍ እውቅና የመስጠት እና ምስጋና የማቅረብ ዝግጅት ዛሬ ግንቦት 8 2016 ዓ.ም በማዕከሉ ተካሄዷል።
ባለፉት ጊዜያት ነፃ የአየር ሰዓት ፣ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ጨምሮ በሚሊዮን ብሮች የሚያወጣ የሚዲያ አገልግሎት ለማዕከሉ እንደተሰጠም ተገልጿል።
ለማዕከሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ የሚዲያ ተቋማት መካከል አርትስ ቲቪ፣ ኦቢኤን ፣ ኢቢሲ ፣ ኤፍቢሲ፣ኢቢኤስ፣አሻም ቲቪ ፣ ትርታ 97.6፣ ቲቪ 9 ፣ አሚኮ፣ አሐዱ ሬድዮ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
በፕሮግራሙ ላይም በኢትዮጵያ ከ 7ሺ በላይ የልብ ህሙማን ህፃናት ወረፋ እየጠበቁ እንደሆነ እና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሹ ተገልጿል ።
የኢትዮጲያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል በሀገራችን የነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና በመስጠት ላይ የሚገኝ ብቸኛ ተቋም ሲሆን ላለፉት 34 ዓመታት ከ8000 በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና በማድረግ የነፍስ አድን ሥራዎችን እንዳከናወነ ተገልጿል።
ማዕከሉ ሁሉንም የሕክምና ወጪዎች ያለምንም ክፍያ በነጻ እንደሚያከናውን የገለፅ ሲሆን አስፈላጊ ወጪዎችንም በዋነኛነት ከማሕበረሰቡ በሚሰበሰብ ዕርዳታ በተጨማሪ ደግሞ ከሀገር በቀል እና የውጪ ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ በመሸፈን ላይ እንደሚገኘ ተነግሯል።
Via – ኢቨንት አዲስ