የድምፃዊ ለምለም ሐይለሚካኤል ”ማያዬ” የተሰኘ የበኩር አልበዋ ሊወጣ ነው፡፡
ተዋናይት እና ድምፃዊት ለምለም ሐ/ሚካኤል አዲስ የበኩር አልበም ከዘጠኝ አመት በኃላ “ማያዬ ” የተሰኘ አልበም ወደ ህዝብ ሊደርስ መሆኑ ተሰምቷል ፡፡
የድምፃዊት ለምለም ሐ/ሚካኤል አልበሙ ወደ 12 ክር ያሉት ሲሆን ለየት ያሉ ስልተ ምቶች ጋር ታጅቦ የቀረበ መሆኑን እና የተለያዩ አንጋፋ እና ወጣት ከያኒያን የተሳተፉበት ሲሆን ከዛ ውስጥ በሕይወት የሌለው አንጋፋው አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ይገኝበታል ተብሏል ፡፡
አበጋዝ ክብረወርቅ ፣ ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ) ፣ ታምሩ አማሩ/ሚኪ ጃኖ/፣ አዲስ ፍቃዱ ፣ ብሩክ ተቀባ በቅንብር ሲሳተፉ በግጥም በዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ አብታሙ ቦጋለ ፣ አንተነህ ወራሽ ፣ ብስራት ሱራፌል ፣ እሱባለሁ ይታየው የሺ ፣ ወንደሰን ይሁብ ፣ ጥላሁን ሰማው ፣ ዘርአ ብሩክ ተሳትፈዋል ፡፡ ሚኪስንግ ፣ ማስተሪንግ ሰለሞን ሀይለማርያም በፕሮዲውሰርነት ወንደሰን ይሁብ ተሳትፈዋል ፡፡
የሚዳስሰው ትዳር ፣ ፍቅር ፣ እናትነት እና የመሳሰሉት በዚህ አልበም ላይ ሲኖር በኦሮምኛ ቋንቋ የተሰራ የተሰራ ሙዚቃም እንዳለ ተጠቁሟል ፡፡
አልበሙ በዚህ ወርሀ ውስጥ አርብ ግንቦት 9/2016 አመተ ምህረት በናሆም ሪከርድስ በኩል እንደሚደርስ ዛሬ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም በማርዮት ሆቴል በሰጠችሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፃለች፡፡
ድምፃዊት ለምለም ሐ/ ሚካኤል የተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ያላት እና በተጨማሪም በሬድዮ በቴሌቪዥን መስኮት የተዉኔት ብቃቷን አሳይታለች ፡፡
Musics, New Releases, Music Videos