አዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች፣ ሳምንታዊ ጉዳይ በሙዚቃው ዘርፍ እና በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም እንደተጠበቀ ሆኖ…
– ተወዳጁ ድምፃዊ ናትናኤል ሃይሌ (ናቲ ሃይሌ) አዲስ ነጠላ ዜማ ይዞ እየመጣ ይገኛል። ይህ ሙዚቃ ግንቦት አንድ እንደ ሚለቅ በራሱ ማህበራዊ ገፅ ላይ ተገልጿል፡፡ ተወዳጁ ድምፃዊ ከዚህ ቀደም “ሌት ይነጋል” የተሰኘ አልበም አውጥቷል። ናቲ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ”በቃ” በተሰኘው ሙዚቃ ነው፡፡
– ድምፃዊትና የግጥምና ዜማ ደራሲ ሃሌሉያ ተክለፃድቅ (ሃሌ ጃኖ) አዲስ የሙዚቃ ስራ ይዛ እንደምትመጣ በራስዋ ማህበራዊ ገፅ ላይ ገልፃለች። ሃሌሉያ የተለያዩ ነጠላ ዜማዎችና “ተወዳጅ” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ለህዝብ አድርሳለች። ሃሌሉያ አዲስ የሙዚቃ ስራ በቅርቡ አደርሳለሁ ብላለች፡፡
– ተወዳጁ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከሰሞኑ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ይዞ እየመጣ ይገኛል። የሙዚቃው ርዕስ “አይ ዕድል” ይሰኛል፡፡ ግጥምና ዜማው የያሲን መሀመድ፣ ቅንብሩ የኪዲ አድማሱ እንዲሁም የቪዲዮው ዳይሬክተር አማኑኤል ገብረመድህን (አቡሽ) ነው።
– ወርቅአፈራሁ ከበደ “ቺቻ” የተሰኘ ሙዚቃ ከሰሞኑ ያወጣል። ግጥምና ዜማው በራሱ በድምፃዊው ሲሰራ ቅንብር፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ስማገኘሁ ሳሙኤል ሰርቶታል።
* የአልበም ጥቆማዎች…
– የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ድምፃዊ አንተነህ ወራሽ በቅርቡ አዲስ አልበም ይዞ እየመጣ ይገኛል። የአልበሙ ርዕስ ”ምሳሌ” ይሰኛል። ይህ አልበም በፕሮዲዩሰሩ ምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት በኩል ለረዥም ጊዜ ሲተዋወቅ ቆይቶ በቅርቡ ለአድማጮች ይደርሳል ተብሏል።
– ሳክስፎኒስት እና አቀናባሪ እንዲሁም ፕሮዲዩሰር ጆርጋ መስፍን አዲስ አልበም በቅርቡ እንደሚያደርስ ታውቋል፡፡ የአልበሙ ርዕስ ‘ከሁሉ የላቀው ደግ’ ይሰኛል። የአልበሙ ስራዎች መንፈሳዊ ውህድ ያላቸው በኢትዮ ጃዝ ስልት የተቃኙ ናቸው። አልበሙ ግንቦት 16 በሙዚቃዊ ዩቲዩብ ቻናል እና የሙዚቃ መተግበርያዎች ላይ ይለቀቃል።
– 13ኛው ለዛ አዋርድ ከሀምሌ 13/2013- ሰኔ 30/2015 ዓ.ም የወጡ የኪነጥበብ ስራዎች በውድድሩ አሳትፎ በቅርቡ ይከናወናል። በ13 ዘርፎች እጩ የሆኑት በምርጥ አዲስ ድምፃዊ/ት፣ ምርጥ አልበም፣ ምርጥ የቴሌቪዥን ተዋናይ እና ተዋናይት፣ ምርጥ ነጠላ ዘፈን፣ ምርጥ ተዋናይ/ት በመሳሰሉት የኪነጥብብ ስራዎች በየዘርፉ አምስት አምስት እጩዎች ቀርበውም ነበር። በስተመጨረሻም የድምፅ አሰጣጡ ተጠናቆ በደመቀ ስነ ስርዓት በሂልተን ሆቴል ግንቦት 16 ይከናወናል ተብሏል።
* በሙዚቃው ዘርፍ ሳምንታዊ ክስታዊ ጉዳይ…
– የበጎ አድራጎጎት አምባሳደር እና አንጋፋዋ ድምፃዊት ቻቺ ታደሰ “ደርሷል ሰዓቱ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ከአስር ዓመታት ቆይታ በኋላ አድርሳለች። ሙዚቃው የሚያጠነጥነው የሰላምን ጥሪና ፍለጋ ወደ ፈጣሪ የምንማልድበትና የምንጮኽበት፣ ተስፋና ፍቅር የምንመኝበት ሃሳብ ላይ እንደሆን ተገልጿል። ሙዚቃውን ለማጠናቀቅ ሶስት ቀናት ብቻ ፈጅቶበታል ተብሏል። በግጥምና ዜማ ቻቺ ታደሰ እና ወንድሟ ደረጄ ታደሰ ሲሳተፉ በቅንብር ሩፋኤል ወልደማርያም፣ ማስተሪንግና ሚክሲንግ ደግሞ ኬኒ አለን ሰርተውታል። ሙዚቃው በቻቺ ታደሰ ዩቲዮብ ቻናል ተለቋል፡፡
– ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮ አልያስ ፍራንስስ (ነጋሪት ባንድ) አልበም በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል “ነጋሪት ባንድ” የጃዝ የሙዚቃ አልበም ታላላቅ እንግዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የሙዚቃ ወዳድ ህዝብ በቦታው በመገኘት ቅዳሜ እለት 19 /2016 ዓ.ም:: በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ውስጥ ተከብሮ ውሏል ።ድራመርሲት ተፈሪ አሰፋ ፣ ሳክፎኒስት ጆርጋ መስፍን ፣ ጊታሪስት አብይ ተክለማርያም እንዲሁም ድምፃዊት ዮሀና ፣ መራዋ ኳየር እና የተመስገን ልጆችም ዝግጅቱን ድምቅ አድርገውታል፡፡
– ተወዳጁ ድምፃዊና የዜማና ግጥም ደራሲ አብዱ ኪያር አምስተኛ አልበሙን በቅርቡ ለአድማጮች እንደሚያደርስ በማህበራዊ ገፁ ላይ ገልጿል። አብዱ ኪያር የመጀመርያ አልበሙ “መርካቶ ሰፈሬ”፣ ከዚያም በመቀጠል “ምነው ሸዋ”፣ “ፍቅር በአማርኛ” በስተመጨረሻ “ጥቁር አንበሳ” አልበሞችን ለህዝብ አድርሷል።
በየኔ ቫይብ በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም…
– የአንጋፋዋ ድምፃዊት ሐመልማል አባተ “ጊዜ ሚዛን” የተሰኘ አልበም ይህ አልበም በርካታ ስሜትን ያዝ የሚያደርጉ ሙዚቃዎች በውስጡ ይዟል። ልኑር፣ ፍታኝ፣ ዋነሚቴ፣ አንዳንዴ ይሆናል ያሉት፣ አሞቦ፣ የጎንደር ጉብል የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።
በግጥምና ዜማ የተሳተፉት ሞገስ ተካ፣ ተስፋ ብርሀን፣ ሙሀሙድ አህመድ፣ ከበደ ለማ እና ተመስገን ተካ ሲሆኑ በቅንብር አበጋዝ ክብረወርቅ፣ ሳክስፎኒስት ጆርጋ መስፍን፣ ቤዝ ጊታሪስት ሄኖክ ተመስገን፣ ሊድ ጊታሪስት ግሩም መዝሙርን የመሳሰሉ በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን ተሳትፈዋል።
@biggrs @yenevibe