አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ክስተት እንጠቁም ፡፡- አንዱአለም ጎሳ- ቢሊሌ(bilillee) የተሰኘ ሙ…

Reading Time: 2 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ክስተት እንጠቁም ፡፡

– አንዱአለም ጎሳ- ቢሊሌ(bilillee) የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን ግጥሙን ሌሊሳ እንድሪስ ዜማ በድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ሲሰራ ቅንብሩን ስማኘየሁ ሳሙኤል(ዲታ ስቱዲዮ)፡፡

– ሞይቦን ተስፋዬ- በከልቻ በሪ”Bakkalcha Barii” የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን ግጥም ዜማ በራሱ ሞይቦን ተስፋዬ የተሰራ ሲሆን ቅንብሩን ቢናንዴ ሰርቶታል ፡፡

-ሰለሞን ፀጋዬ -አንቺን ሳይ የተሰኘ ሙዚቃ በሆፕ ኢንተርቴመንት በኩል ረቡዕ ይለቀቃል ቢባል እስካሁን አልተለቀቀም በቅርቡ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

– ጣሳው ወንድም – የትንፋሽ ውበት የተሰኘ በዋሽንት /በፍሉት/ ብቻ የተቀነባበረ አልበም ለቅምሻ ማድረሱ አይዘነጋል በአልበም ከፍ ብሎ እየመጣ ይገኛል አልበሙ በራሱ ዩትብ ቻናል የሚለቀቅ ሲሆን (tasaw wendim) ብላችሁ ቅምሻውን እና አልበምን ሲለቀቅ መስማት ትችላላችሁ ፡፡

አልበሙ ላይ ፒያኖ ቀረፃ እና ሚክሲንግ ዓብይ ወልደ ማርያም ፐርክሽን ተፈሪ አሰፋ ክራር ቢኒያም ዳኛቸው ቤዝ ጊታር እዮሲያስ ታመነ እና ሌሎችም ተሳትፈዋል ፡፡

* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት እናንሳ

-የግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም አቀናባሪ ተዋናይ  አማኑኤል ይልማ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ዝግጅት ፕሮግራም ፣ የፊልም ፅሁፍም ተሳትፎ እንደ ሚፈልግ እና ከተወዳጁ ቴዲ አፍሮ ቴዎድሮስ ካሳሁን ግርማሞ ጋር አዲስ አልበም አብረው እየሰሩ መሆኑን በዚህ ሳምንት የሰማነው ነው፡፡

አቀናባሪ አማኑኤል ይልማ አብረው ከሰሩ አንጋፋ ድምፃዊያን ያለውን አድናቆት እንዲሁም ችሎታቸውን አንስቶ በቀጣይም እንዲህ ያሉት አዳዲስ ባለ ተስዖጦ ወጣት ድምፃዊያኖች ጋር በአዲስ ስራ እየመጣ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

– አቀናባሪ የባላገሩ ምርጥ ዳኛ ሱልጣን ኑሪ(ሶፊ) ላበረከተው ሙዚቃዊ አስተዋፅኦ በበዓሉ ለት ተመስግንዋል፡፡ ከ መቶ አያ (120) በላይ የኢትዮ አሜሪካ ዲፕሎማሲ ግንኙንነት ክብረ በዓል አስመልክቶ ተወዳጁ አቀናባሪ ሱልጣን ኑሪ (ሶ) ማሲንጋ የተሰኘ ሙዚቃ ስራዎች አቅርቧል ፡፡

አቀናባሪ ሱልጣን ኑሪ በኢትዮጵያ የሚሰሩ ፊልሞች ላይ ሳውንድ ትራክ ( የፊልም ማጀብያ) የሰራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ዓባይ ወይስ ቬጋስ ፣ ሲመት ፣ አይገባንም ፣ብላቴና እና የመሳሉት ሰርቷል የቴሌቪዥን የፕሮግራም መግቢያ የሰራ ሲሆን ፋና ቀለማት ፣ ፋና ዘጠና ኢንትሮ መግቢያ አበርክቷል ፡፡ በሙዚቃው ከ አቡሽ ዘለቀ ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ መሀመድ ሲርጋጋ የብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው ፡፡

– ድምፃዊ ሳሙኤል ብርሀኑ (ሳሚ ዳን ) አምስተኛ አልበም ” መልኬ” እየሰራ መሆን ገልፆ አዲስ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ስቱዲዮ እና ሙሉ ቀረፃም ማድረግ የሚያስችል ቦታ እንደገባ በዚህ ሳምንት የሰማነው ክስተት ነበር ፡፡ የስቱዲዮ ስያሜ ”ሩፍታፕ ሚውዚክ ”ብሎ የሰየው ሲሆን በዚህ ስቱዲዮ መጪዎች ወጣት ድምፃዊያኖችን በአዲሱ ስቱዲዮ ማፍለቅ የሚጀምር ሲሆን ሳሚ ዳን ከዚህ በፊት የተነሳበትን የሙዚቃ ጉዞውም አስታውሷል ፡፡

ድምፃዊ ሳሙኤል ብርሀኑ  (ሳሚ ዳን) የመጀመርያ አልበሙን ከራስ ጋር ንግግር ፣ 11ዱ ገፆች ፣ ስበት እንዲሁም ቅፅበት ሲል አልበም አድርሷል ይህ አልበም በአቀናባሪ አንዱዋለም ቤተ ( ኤንዲቤተ ዜማ) ተሰርቷል ፡፡ ሳሚ ዳን አዲስ አልበም መልኬ የተሰኘ አምስቱኛ አልበም እየሰራው ነውም ብሏል ፡፡

– አስቻለው ፈጠነ ( አርዲ) በህዝብ ዘንድ በይበልጥ ተወዳጅነትን ያተረፈው የባህል ሙዚቃ ተጫዋች የይበልጥ የታወቀበት ሙዚቃ እናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም የዚህ አቀናባሪ እስራኤል መስፍን በኮራ አዋርድ ሙዚቃ ዘርፍ በአንደኝነት እመራ መሆን በማህበራዊ ገፁ ላይ ገልፆ ነበር፡፡

አሁንም ፉክክሩ እንደ ቀጠለ ሲሆን ገብቻችሁ መምረጥ ትችላላችሁ ፡፡ በኮራ አዋር ወደ 20 የሚጠጉ ሙዚቃ ዘርፍ የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ መካከል ድምፃዊ አስቻለሁ ፈጠነ አርዲ ይገኝበታል ፡፡

– በዚህ ሳምንት ካጣናቸው አንጋፋ ድምፃዊያን መካከል ጥላሁን ገሰሰ ይገኝበታል ሚያዝያ 11/2001 ታላቁን ድምፃዊ ያጣንበት ነበር፡፡

– ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ በኢትዮጲያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አበርክቶ ያለው ሲሆን ዘመን የማይረሳው ታሪክ አቁሟል በ68አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

* የኔ ቫይብ በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ ሙዚቃ…

– የቴዎድሮስ ምትኩ ” የቴዲ ስሜት” በሙዚቃ መሳርያ የተቀነባበረ ብቻ ሲሆን ይህ አልበም 1990ዎቹ መጨረሻ በሰሜን አሜሪካ በስፋት ይገኝ ነበር፡፡ ሙዚቃዊ ቅንብሩ ዓለም አቀፍ ይዘት የያዘ ሲሆን የቴዲ ስሜት የተሰኘው አልበም ላይ የተሳተፊ አበጋዝ ክብረወርቅ ፣ሄኖክ ተመስገን ፣አማን አድነው እና የመሳሰሉት አልበሙን አቁመውታል ፡፡

@yenevibe
https://t.me/yvposts
130410cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ክስተት እንጠቁም ፡፡- አንዱአለም ጎሳ- ቢሊሌ(bilillee) የተሰኘ ሙ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE