“አዲስ ታለንት ሾው” የሚል የኪነ-ጥበብ ውድድር ሊጀመር ነውአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአይነቱ ለየት ያለና የመ…

Reading Time: < 1 minute
“አዲስ ታለንት ሾው” የሚል የኪነ-ጥበብ ውድድር ሊጀመር ነው

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአይነቱ ለየት ያለና የመዝናኛው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ የሚያመጣ አዲስ ታለንት ሾው የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ውድድር በቅርቡ እንደሚያስጀምር አስታወቀ።

ተቋሙ በሁሉም የሚዲያ ዘርፎች ተወዳዳሪ ተመራጭና ተደራሽ የሚያደርገውን አቀራረብና ይዘት ወደ አድማጭ ተመልካቾች እያደረሰ ይገኛል።

የመዝናኛው ዘርፍ ተወዳዳሪነትን ከፍ የሚያደርግ ነዉ የተባለዉ “አዲስ ታለንት ሾው” በቅርቡ ለማስጀመርም ተቋሙ ዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

ታለንት ሾውን ለማስጀመር የሚያስችል የውይይት መድረክም ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል።

በዚሁ ጊዜ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የቴሌቪዥን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ እንዳሉት የኪነ ጥበብ ውድድሩ ሚዲያውን በመዝናኛው ዘርፍ ተምሳሌት የሚያደርገው ነው ብለዋል።

የታለንት ሾው ውድድሩ አዲስ ክስተትና ለውጥ የሚያመጣ ፣በአዳዲስ ስራዎች የሚቀርብ፣ የአሁኑ ትውልድ የራሱን ቀለምና ታሪክ ይዞ የሚቀርብበት መሆኑንም አውስተዋል።

የታለንት ሾው ውድድሩ ሙዚቃን ጨምሮ ሁሉንም የኪነ ጥበብ ስራዎች ያካተተ ሲሆን ከፍተኛ ሽልማቶችንም የሚያስገኝ ነው ተብሏል።

አዲስ ታለንት ሾው የከተማዋ ነዋሪዎችን የሚያሳተፍና ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ የቴሌቪዥን የኪነ ጥበብ ውድድሮች ከሚያዘጋጁት የአሸናፊዎች ሽልማት የላቀ ገንዘብ እንደተዘጋጀም ተመልክቷል።

የአዲስ ታለንት ሾው ዳኛና አዘጋጅ አርቲስት ማህሌት ሰለሞን በበኩሏ ሾው አዲስ እይታ ፣አዲስ አቀራረብና ሀሳብ የሚስተናገድበት ነው ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ ታሪክና ለውጥ በኪነ-ጥበብ ስራዎች ይገለጻሉም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ በፍቃዱ መለሰ

@yenevibe
127420cookie-check“አዲስ ታለንት ሾው” የሚል የኪነ-ጥበብ ውድድር ሊጀመር ነውአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአይነቱ ለየት ያለና የመ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
Surafel

Surafel

Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly.
Surafel

Surafel

Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly.

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE