ድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ በዘንድሮ ዓመት የበኩር አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንደሚያበቃ ገለፀበተለያዩ ነጠ…

*
ድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ በዘንድሮ ዓመት የበኩር አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንደሚያበቃ ገለፀ

በተለያዩ ነጠላ ዜማዎች ከሙዚቃ አፍቃሪያን ጋር የተዋወቀው ወጣቱ ድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ ‹‹ባለክራሩ›› በተሰኘው ፊልም ላይ በክራር ብቻ ያቀነቀናቸውን የሙዚቃ ስራዎች ስብስብ በአዲስ መልክ መስራቱን አሳውቋል፡፡

በክራር የሙዚቃ መሳሪያ ብቻ ታጅቦ ያቀነቀናቸው የቀደሙ ስራዎችን ጨምሮ ለፊልሙ የተዘጋጀ አንድ ሙዚቃን ጨምሮ በድምሩ አምስት ስራዎች እንደሆኑ ታውቋል፤ ድምፃዊው ከእዚህ ቀደም ‹ህዳር› በተሰኘው ፊልም ላይ ባቀነቀነው የማጀቢያ ሙዚቃ አማካይነት በጉማ አዋርድ ላይ ተሸልሞ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ድምፃዊው ስለ አዲስ አልበሙ ለተነሳለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽ ቢቻል በእዚህ ዓመት አጋማሽ፤ ካልሆነ በ2017ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ ሀሳብ እንዳለው አስታውሷል፡፡

የአልበም ስራው ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ሊያስቆጥር ተቃርቧል ያለው ድምጻዊው በስራው ላይ ተሳትፎ ስላደረጉ ባለሙያዎች ባይገልፅም ብዙ ፈተናዎችን አልፎ ቢሆን ለሙዚቃ ወዳጆች የማድረስ ሃሳብ እንዳለው ገልጿል፡፡
158730cookie-checkድምፃዊ ሙሉዓለም ታከለ በዘንድሮ ዓመት የበኩር አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንደሚያበቃ ገለፀበተለያዩ ነጠ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE