ለአልፋ መስማት ለተሳናቸው ልዩ ትምህርት ቤት የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።ከተመሠረተ ከ58 አመት በ…

Reading Time: < 1 minute
ለአልፋ መስማት ለተሳናቸው ልዩ ትምህርት ቤት የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ከተመሠረተ ከ58 አመት በላይ ያስቆጠረው እና "እጆች ይናገራሉ ፣አይኖች ያደምጣሉ "የሚል መሪ ቃል ይዞ የተነሳው አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ ትምህርት ቤት ለ6 ወር የሚቆይ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ፣ 50 ደርዘን ደብተር ፣ የትራንስፖርት ወጪ እና ለተማሪዎቹ የእጅ ሙያ ሥራ ግብዓት የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ከአይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል አበረከተ።

በአዲስ አበባ ብቸኛ የሆነው አልፋ መስማት የተሳናቸው ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት 125 ተማሪዎችን ከቅድመ መደበኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ተቀብሎ እያስተማረ የሚገኝ ሲሆን ተማሪዎቹ ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር የእጅ ሙያ ሥራ እንዲሰለጥኑ እየሠራ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ከበብሽ በቀለ በስጦታው ርክክብ። መርሐግብር ላይ ገልጸዋል።

ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንጻር በርካታ ስራዎችን መስራቱን ያነሳው እና ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የዚህ መርሐግብር አንዱ መሆኑን አይ ሲ ኤም ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል አሳውቋል።
97540cookie-checkለአልፋ መስማት ለተሳናቸው ልዩ ትምህርት ቤት የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።ከተመሠረተ ከ58 አመት በ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE