የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ 2016/2024 ኦፕን ቶርናመንት ሊካሄድ ነው
የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከሳኦል ኩነቶች አዘጋጅ ጋር በጋራ በመኾን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ /2024 ኦፕን ቶርናመንት ከግንቦት 3 እስከ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የሚካኼደው በዚሁ ውድድር ከአንድ ሺህ በላይ ተወዳዳሪዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ውድድር ብቃት ኖሯቸው የውድድር መስክ ያጡ ኢትዮጵያዊውያን በኦንላይን ማመልከት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ዋሲሁን እንደተናገሩት “ይህን ስፖርት በጋራ ለማሳደግ ማህበረሰቡን ወጣቱን፣ ሴቶችን፣ ህፃናትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው የግልና የመንግስት ተባባሪ አካላት እጅ ለእጅ ተያይዘው በጋራ መስራት ያስፈልጋል” ብለዋል። ሁነቱን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የማስተባበር ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኘው የሳኦል ኩነቶች አዘጋጅ አቶ ዳዊት ደረጄ ተመስግነዋል።