የድምፃዊት ህብስት ጥሩነህ ተጣልተናል ወይ? በየወሩ እንደምናመሰግነው ወሩ ደርሶ አመስግነናል ፡፡
የምንጊዜም ተወዳጅ አልበም ነው በባህል ዘመናዊ ተከሽኖ የተሰራ ኤልያስ ፍቅሩ(ናሆም ሪከርድስ) ፕሮዲውስ የተደረገው ተጣልተናል ወይ? አልበም በጥያቄ ውስጥ የሚመላሰስ መልሱን በራሳችን ልኬት የምንመነዝርበት አልበም ነው ፡፡
ድምፃዊት እብስት ጥሩነህ የራስዋ ቀለም ፣ በተለየ የቴክኒክ አረዳድ ፍንትው ብሎ የወጣበት እና የችሎታዋ ጥግ በማይጠገበው ድምጿ ያሻገረችበት አልበም ነው ፡፡
በዚህ አልበም ብዙ ነገር ለመግለፅ ሞክራለች ለምሳሌ ለመጥቀስ … ነገር ካመለጠ በኃላ ጥበቃው ትርፍ መሆኑ የቃል ኪዳን አርፋጅ ዋጋ እንደሚስከፍል ፣ ሁሉንም እሺ ማለት ሳይሆን መመርመር ልባችን ቢፈቅድ እንኳን በአስተውሎት በመጓዝ ፣ ማፍቀር እና መፈቀርን ፣ ወኔ ፣ ተስፋን ፣ ፍቅርን ፣ እምነትን ፣ በፅኑ መናፈቅን በአልበሙ ተንፀባርቀዋል፡፡
አልበሙ ውስጥ 14 ክሮች ያሉት ሲሆን መምጣቴ አይቀርም ፣ ወፍ ሳይንጫጫ ፣ ድነሀል ፣ ለየለት ፣ ታገሰኝ ፣ ጓደኞቼ ፣ ይነጋል ፣ ከመሸህ መጣህን የአልበሙ መጠርያ ተጣልተናል ወይ ? ጨምሮ የመሳሰሉት በአልበሙ ተካተዋል ፡፡
ከ መሸህ መጣህ…
“ምነው ከመሸ መጣህ ቀኑ ካለፈ
ደጄ ቄጤማው ደርቆ እሾክ አረፈ
አንተ በአንድ ቃል ኪዳን ሁሉት ቤት ሰሪ
ምነው ደርሶ መሆንህ ማተበ ሰሪ”…
ግጥም ተመስገን አፈወርቅ ዜማ ብስራት ጋረደው ቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፡፡
ታገሰኝ …
“በእርግጥ አመንኩት እንደሱ ሲሆን እፈራለሁ
ነገር ሲዋከብ ከስሩ መመርመር እሻለሁ
እኔ አልችልም እኔ አላውቅም ሰው መላመድ ፈጥኜ
ተይዞ ታምቄ ልከተልህ አምኜ” …
ግጥም እና ዜማ ድምፃዊ እንዳለ አድምቄ ቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፡፡
በአልበሙ የተለያዩ የጥበብ ከያኒያን ሲሳተፉ እንዳለ አድምቄ ፣ ተመስገን አፈወርቅ ፣ ብስራት ጋረደው ፣ ይስማዓለም አረጋ ፣ የማንዶሊን አለቃ ጋሽ አየለ ማሞ ተሳትፈውበታል ፡፡
በቅንብር ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ ሙሉ በሙሉ አልበሙን አጠናቆ ሰርቶታል ፡፡
የኔ ቫይብ ስለ ሰጣችሁም ውብ አልበሙ በዚህ አልበም እጃችሁ ያረፈበት ሁሉ ከልብ እናመሰግናችኃለን ፡፡