“መቅደስ የልጆች አድማስ” በይፋ ሥራ መጀመሩ አበሰረበአርቲስት መቅደስ ጸጋዬ መስራችነት በአንድ ቢሊዮን ብር…

Reading Time: < 1 minute
*
“መቅደስ የልጆች አድማስ” በይፋ ሥራ መጀመሩ አበሰረ

በአርቲስት መቅደስ ጸጋዬ መስራችነት በአንድ ቢሊዮን ብር “መቅደስ የልጆች አድማስ” የተሰኘ የወላጅ አልባ ልጆች ማዕከል ለሟቋቋም የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ እና ስራ የማስጀመሪያ መርሐግብር በስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ማምሻውን ተካሂዷል።

ድርጅቱን ለማቋቋም ሃሳቡ የተፀነሰው ከ6 ዓመታት በፊት እንደሆነ የድርጁቱ መስራች አርቲስት መቅደስ ጸጋዬ በመርሐግብሩ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ገልጻ ድርጅቱ በዋናነት ልዩ ትኩረት እና ጥበቃ ለሚያስፈልጋቸው ወላጅ አልባ ህፃናት ልጆች አስፈለጊውንና ሁሉን አቀፍ እንከብካቤ በመስጠት በቀጣይ የሕይወት ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደታሰበ ገልጻለች።

በገቢ ማሰባሰቢያ እና ስራ የማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስተር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ማዕከሉን ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቤቱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጸው፤ ማዕከሉ እውን እንዲሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እና የግል እና የመንግስት ተቋማት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

“መቅደስ የልጆች አድማስ” የመጀመሪያ ተቋሙን የሚገነባውና ስራውን የሚጀምረው በአዲስ አበባ ሲሆን ቀስ በቀስም ወደ ሌሎች ክልሎች ቅርንጫፎቹን የሚያሰፋፋ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 200 ህፃናትን ከመላው ኢትዮጵያ የሚቀበል እና ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ደግሞ 1000 ህፃናትን የመቀበል አቅም እንደሚኖረው በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።
94660cookie-check“መቅደስ የልጆች አድማስ” በይፋ ሥራ መጀመሩ አበሰረበአርቲስት መቅደስ ጸጋዬ መስራችነት በአንድ ቢሊዮን ብር…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE