የቤተልሔም ታፈሰ ሁለተኛ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ተመረቀ። የቀድሞ “ኤል ቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በ…

Reading Time: < 1 minute
*
የቤተልሔም ታፈሰ ሁለተኛ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ተመረቀ።

የቀድሞ “ኤል ቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በነበሩ አነጋጋሪ ቃለ መጠይቆቿ የምትታወቀው ቤተልሔም ታፈሰ  የኢትዮጵያ ፖለቲከኞችን ታሪኮች የያዘ “አምስት ጉዳይ” የተሰኘ ሁለተኛ መጽሐፏን በራማዳ ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ተመርቋል።

በ 5 ምዕራፎች እና 220 ገጾች በተዘጋጀው በዚህ መጽሐፍ፤ እንደ መጀመሪያ ስራዋ ሁሉ የጃዋር መሐመድ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ሌንጮ ለታ ታሪኮች ተካትተውበታል።

ቤተልሄም ከዚህ ቀደም ባሳተመችው “እኔ እና የኤልቲቪ ምስጢሮቼ” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ያልነበሩት፤ ልደቱ አያሌው እና ነአምን ዘለቀ በአዲሱ መጽሐፍ ቦታ የተካተቱ ሲሆን በ400 የኢትዮጵያ ብር ለአንባቢያን ቀርቧል።
84920cookie-checkየቤተልሔም ታፈሰ ሁለተኛ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ተመረቀ። የቀድሞ “ኤል ቲቪ” ቴሌቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE