ሴንቼሪ ፕሮሞሽንና ኢቨንትስ «ሠላም የፋሲካ በዓል ባዛርና ፌስቲቫል» ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
የተለያዩ ባዛርና የንግድ ትርዒቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ሴንቼሪ ኘሮሞሽን እና ኢቨንት ከሚያዝያ 5 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ22ቀናት የሚቆይ « ሠላም የፋሲካ የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል» በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ።
25ኛ አመት የምስረታ በዓል በማክበር ላይ የሚገኘው ሴንቼሪ ኘሮሞሽን እና ኢቨንት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ በመጪው የፋሲካ በዓል አስመልክቶ ከ4 – 6 ካ.ሜ ለሆነ ቦታ የቫት የድንኳን ኪራይ እና ሌሎች አገልግሎቶችን አጠቃሎ ለ22 ቀናት ከ50,000 ብር ጀምሮ እንዲሳተፉ እድል ማመቻቸቱን ገልጸዋል።
በኤከሰፖው ላይ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ምርት እና አገልግሎቶች፣ የባንክ እና የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የሪል እስቴት አልሚዎችና የኢንሹራንስ ሽያጭ እከናዋኞች፣ የምግብና መጠጥ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የቤትና የቢሮ እቃዎች አምራችና አስመጪዎች እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች እንደሚሳተፉ የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማነህ ገልጸዋል።
በዚህ ለ33ኛ ጊዜ በሚዘጋጀው የፋሲካ ንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል አዲስ የስራ ፈጣዎች እና አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ልዩ ድጋፍ በማድረግ በአቅማቸው እንዲሳተፉ ለማስቻል መታቀዱን አቶ ዘውገ ጀማነህ ጨምረው የገለፁ ሲሆን በአማካይ በቀን እስከ 15 ሺ የሚደርሱ ጎብኚዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚታሰብም ገልጸዋል።
ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ባለፉት 25 ዓመታት በአጠቃላይ ከ75 የሚበልጡ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ዝግጅቶችን ማሰናዳቱን መቻሉ ተገልጿል።