አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ጥቆማ ፣ ክስተታቸውን እንጠቁም…- ደቤ አለምሰገድ -ልዋልበት የተሰኘ ነጠ…

Reading Time: 2 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ጥቆማ ፣ ክስተታቸውን እንጠቁም…

– ደቤ አለምሰገድ -ልዋልበት የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ሲሆን በግጥም እና ዜማ ራሱ ደቤ አለምሰገድ ሰርቶታል በቅንብሩ ተወዳጁ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ነው ፡፡

– ልዑል ሀይሉ – እሳቱ ሰዓት አልበሙ በበርካቶች ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን አልበሙ ከወጣ ቢቆይም እንደገና በናሆም ሪከርድስ በኩል ይጫናል ፡፡

2011 በበገና እቱዲዮ የበቀለው አልበሙ እሳቱ ሰዓት አልበም በግጥሙ ኤልያስ መልካ ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ በቅንብር እና ዜማ እንዲሁም ግጥም ኤልያስ መልካ ሰርቶታል በውስጡ 13 የሙዚቃ ክር ሲኖሩት አዲስ አለም ፣ ጅል ትግስት አለ ፣ የቀነስኩላት ከ ምቾቴ ፣ ቀዳሚ ምን ተቀዳሚ የመሳሰሉት አሉበት ፡፡

ሙዚቃዊ ጥቆማ

-ፋና ላምሮት አራተኛው የአሸናፉዎች አሸናፊ አስራ ሁለተኛው ሳምንት ወደ ፍፃሜ የሚያልፉት የሚለይበት አምስቱ ተወዳዳሪዎች አጉዋጊው እና እልህ አስጨራሽ ውድድር ያከናውናሉ ቅዳሜ 21/2016 ከስድስት ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ በፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት በፋና ቲቪ እና በተለያዩ ማህበራዊ ገፅ ይከታተሉ ፡፡

– የኢትዮጲያን አይደል ሶስተኛ ምዕራፉን በቅርቡ እንደ ሚጀምር አስታውቋል ባለፉት ሁለት ምዕራፎት በተውኔትም በሙዚቃ ዘርፊ አሸናፊዎችን ሸልሞ እና ወደ ሙዚቃ እንደስትሪ በተጨማሪም ወደ ተውኔታ አለም የቀላቀላቸው አሁን በሶስተኛው ምዕራፍ ይንን ለመድገም እየመጡ ይገናሉ ዳኞች ዝናሽ ሆላኑ ፣ ሰርፀ ፍሬ ስብዓት ፣ ሰራዊት ፍቅሬ እና ነብዩ ባዬ እንደ ተለመደው ተሰይመው ይጠብቋቸዋል ፡፡

የኔ ቫይብ አልበም እንድታዳምጡት የምንጠቁማችሁ ፡፡

-1982 በሌክትራ ሙዚቃ ቤት የታተመው ድምፃዊት አስቴር አወቀን አልበም ግብዣችን ይሁን ወደ አስር የሚጠጉ ሙዚቃዎች ሲኖሩት ከ ሸጋም ሸጋ  ፣ ለመድክ ወይ ፣ የአባይ ልቡ፣እሹሩሩ ፣አካል ሰው ይገኙበታል በግጥም እና ዜማ የተሳተፉት አለምፀሐይ ወዳጆ ፣አስቴር አወቀ ፣አበበ ብርሀኔ ፣አበበ መለሰ ፣ ሶስና ታደሰ ናቸው በቅንብሩ አንጋፋው ደረጄ መኮንን እና አቀናባሪ ጥላዬ ገብሬ ሰርተውታል ፡፡

ሰሞንኛ ሙዚቃዊ  ክስተታዊ ከተወሩት ውስጥ

የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ አልበሙ በተመለከተ …

የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ መንግስቱ(ተገኔ)የመጨረሻ አልበሙ ለህዝብ እንዲደርስ ወደ ስራ ተገብቷል ፡፡

አምስት የሚጠጉ አቀናባሪዎች ጋር የሙዚቃ ስራዎችን እየሰራ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን በአጠቃላይ ወደ አስራ ስድስት የሙዚቃ ክሮችን ሲሰራ ነበር ተብሏል ፡፡

የማዲንጎ አፈወርቅ በሕይወት ሳለ ሲሰራቸው የነበሩት ሙዚቃዎች ወደ መጠናቀቁ የቀረበ ሲሆን የሚቀሩት ቅንብር ፣ ሚክስ ፣ እና ማስተሪንግ ነው ፡፡ አሁን ሙዚቃው ወደ መረጣ የተገባ ሲሆን ከ እስካሁን ከ ወጡ አልበሞች የላቀ ለማድረግ እየጣሩ መሆኑን የሞያ አጋሮቹ ዘላለም መኩርያ ፣ ፋንታ ወጨፎ ናቸው ፡፡

ሙዚቃዎቹ ተመርጠው ወደ ህዝብ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በትናት እለት የዓለም የትያትር ቀን እየተከበረ ነበር ፡፡

እኛ የትያት ጥቆማችን በሀይሉ ግርማ ቤርሙዳን ጋበዝን ፡፡

@biggrs @yenevibe
84560cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ጥቆማ ፣ ክስተታቸውን እንጠቁም…- ደቤ አለምሰገድ -ልዋልበት የተሰኘ ነጠ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE