እንኳን ዓለም አቀፍ የትያትር ቀን አደረሳችሁ…
ቀን 18 /ወር 7/ ዓ.ም 2016 አመተ ምህረት ፡፡
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሰፊዋን ሀገር ፍቅር ትያትርን እንመልከት ፡፡👇
ከዛሬ 88 ዓመታት በፊት ጣልያን ለዳግም ወረራ ተመልሳ ሀገራችንን ለመቆጣጠር ባንዣበበችበት ወቅት ሀገሬን አላስደፍርም በሚል ዓላማ ነበር በሀምሌ 11 1927 ዓም የአዲስአበባ ህዝብ የሀገር ፍቅር ማህበር የተመሰረተው።
በዘመኑ አሉ የተባሉ ምሁራን, አንደበተ ርዕቱዎች, ሰዓሊያን, ባለቅኔዎች አዝማርያንን ጨምሮ ዘውትር እሁድ ከሚኒልክ አደባባይ ወረድ ብሎ ባለ ስፍራ ለተሰበሰበው ህዝብ በሽለላ በፉከራ በቀረርቶ እያዋዙ ህዝቡ ሀገሩ በጠላት እንዳትደፈር ዘብ እንዲቆምላት ይሰብኩ የነበረው።
ይህ የመጣ ጠላት ሳይደርስ ከጠረፍ
ተነሱ እንነሳ ደማችን ይፍሰስ
እንደ ሰኔ ውሃ እንደ ሀምሌ ጎርፍ
ይሂድ ይቀላቀል ከአባይ ጋር ይውረድ
ነፃነት ያጣ ህዝብ አይባልም ወንድ
የስነ ስዕሉ ሰው አገኘሁ እንግዳ ወንዱን ሁላ እንዲህ ሲነሽጡት
ንጋቷ ከልካይ ደግሞ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ግጥምና ዜማውን ባስጠኗት መሰረት አንጀት በሚበላ ድምፅ
አይባባ ልብሽ አይባባ
አዲስ አበባ ልብሽ አይባባ
ማሽላና ስንዴ ባንድ አብረን ስንቆላ
እያረረ ሳቀ የባህር ማሽላ
አይባባ ልብሽ አይባባ
እያለች በአደባባይ የገኘውን ህዝብ ለሀገሩ እንዲሰዋ ትቀሰቅሰዋለች።
በሀገር ፍቅር ስሜት የተቋቋመው የአዲስ አበባ ህዝብ የሀገር ፍቅር ማህበር ከ5 ዓመት የጭንቅ ዓመታት በኋላ በ1933 ሚያዝያ ከፋሺስት ጣልያን ነፃ መውጣት ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፍ የከፈቱ ሲሆን እንደ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ትላልቅ ስራ ”አፋጀሽኝ ተውኔት” እንዲሁም
በሀገራችን የመጀመሪያው በአስራ አራት ሴቶች እና በዘጠኝ ወንድ ድምፃውያን የሚመራ የባህል ኦርኬስትራም ለዕይታ ይቀርቡ ጀመር።
ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑት ስራዎች መሀልም
ለብዙዎች የሀገር ናፍቆት መወጫ
የሽምብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ የትም የትም ዞሬ ትዝ አለኝ ሀገሬ። በጋሽ ጌታመሳይ አበበ
ውብ ሀገሬ ውብሀገሬ ባንቺ እኮ ነው መከበሬ
በጋሽ እዩኤል ዩሀንስ
አያት እናቶቻችንን የዳረ እስከ ቅርብ ጊዜ የሰርግ ማድመቂያ የሆነው ሙሽራዬ ዘፈን በጋሽ በሻህ ተ/ማርያም
እንዲሁም አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ ከዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ እየተባለ ህፃናት ሳይቀሩ የዘመሩለት አዋቂዎች የሙዚቃው ንጉስ እያሉ የሚያሞካሹት ጋሽ ጥሌ ሳይቀር
በሀገር ፍቅር መድረክ ላይ
ኢትዮጵያ ሀገሬ ኩራት ይሰማኛል
ካንቺ መፈጠሬ እያለና ሌሎች ስራዎችንም ቀልፆበታል።
የተለዪ ክስተቶች
እንደ ሙናዬ መንበሩ ዓይነት ለሙያው ትልቅ አክብሮት ያላት አርቲስትም የልጇን ሞት ተረድታ ሀዘኗን ዋጥ አድርጋት ስራዋን ያጠናቀቀችበት
ሞታቸው በመድረክ የሆኑ የቴአትር ቤቱ አርቲስቶች
በላይነሽ ውብአንተ እየዘፈነች ሞቷ በመድረክ ላይ የሆነ
ጊታሪስት ዮሀንስ ጊታሩን እንደያዘ ሞቱ በመድረክ የሆነ…