በአራዳ ክፍለ ከተማ የቴኳንዶ ስፖርት ውድድር ተጀመረ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወርልድ ቴኳንድ ፌደሬሽንና የአራ…

Reading Time: < 1 minute
*
በአራዳ ክፍለ ከተማ የቴኳንዶ ስፖርት ውድድር ተጀመረ

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወርልድ ቴኳንድ ፌደሬሽንና የአራዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር የክበባት ውድድር እየተካሄደ ነው።

ለተከታታይ ሁለት ቀናት በሚቆየው ውድድር ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ስድስት ክለባት እንዲሁም ስድስት ተጋባዥ ክለባት በጥቅሉ 12 ክለባት የሚሳተፉበት ሲሆን በውድድሩ ላይ አራት መቶ በላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

በመክፈቻው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ዋሲሁን እንደተናገሩት “የውድድሩ አላማ የቴኳንዶ ስፖርቱ ላይ ያሉ ተወዳዳሪዎችን ለማነቃቃት፣ ልምድ እንዲቀስሙ፣ በተወዳዳሪዎች ዘንድ የፉክክር መንፈስ እንዳኖር፣ ክለባት ተሳታፊ እንዲሆኑ እና በተለይም ስፖርቱ የኦሎምፒክ ውድድር በመሆኑ ሀገርን የሚወክሉ ብቁ ተወዳዳሪዎች ለማግኘት ይረዳል” ብለዋል።

በስፖርት ዘርፍ ሀገራችሁን ማስጠራት ትችላላችሁ ያሉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይልማ ተረፈ ጊዜያችሁንና እውቀታችሁን በመጠቀም ሀገራችሁን ልታገለግሉ ይገባል ብለዋል፡፡
84340cookie-checkበአራዳ ክፍለ ከተማ የቴኳንዶ ስፖርት ውድድር ተጀመረ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወርልድ ቴኳንድ ፌደሬሽንና የአራ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE