አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እና ሳምንታዊ የሙዚቃ ክስተታዊ እንዲሁም ጥቆማ እናድርሳችሁ ፡፡
– ናሆም የማነ – እንደ እኔ ነሽ ወይ? የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን ግጥም እና ዜማ (job 27) በጆፕ 27 በትክክለኛ ስሙ እዮብ ሲሰራው ቅንብሩን ቢኒያም አማረ (ቤንጃ) ሰርቶታል ፡፡
– ተሙ (tofan) – ነይልኝ የተሰኘ ሙዚቃ ሰሞኑን በኑና ፕሮዳክሽን በኩል አድርሶናል ግጥም እና ዜማ ዊዝ ናታን ቅንብር በሉላ ማን ሲሰራ ማስተሪንጉን ኪሩቤል ተስፋዬ ከውኖታል ፡፡
– ባልከው አለሙ እና ስንታየሁ በላይ -” ከ ሐሳቤ” የተሰኘ ሙዚቃ (በሙ ዚቃዊ) ዩትዮብ ቻናል በኩል አርብ ያደርሱናል ከዚህ ቀደም ባልከው አልሙ እና ስንታየሁ በላይ( ኢፒ) ግማሽ አልበም ሰርተው ለህዝብ ማድረሳቸው ይታወሳል ፡፡
-ድምፃዊት ሐሊማ አብዱራህማን -የኔ ተስፋ የተሰኘ አልበም ወደ ህዝብ ለማድረስ እየሰራች ትገኛለች ይህ አልበም ስያሜው ቆየት ያለ ብሆንም በአልበም በኩል በቅርብ ቀን ይደርሳል ፡፡
* ሙዚቃዊ ጥቆማ…
– ለክቡር ዶክተር አርቲስት የጃዝ አባት ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ከ አድናቂዎቻቸው ጋር የሚገኙበት ቀን ተመቻችቷል መጋቢት 14/2016 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል በእለቱም የምስጋና እና የክብር ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
– ፋና ላምሮት አራተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ግማሽ ፍፃሜ ማለትም በአስራ አንደኛ ሳምንት ስድስት ተወዳዳሪዎች ይዞ ከ ዛይን ባንድ ጋር ውድድራቸውን ያከናውናሉ ቅዳሜ 14/2016 ዓ.ም በቀጥታ በፋና ቲቪ ከ ስድስት ሰዓት ጀምሮ መከታተል ትችላላችሁ ፡፡
– ደሞ አዲስ በአዲስ ዋልታ የሚተላለፈው የባለ ተስዕጦህ ውድድር በመጋቢት እሁድ 15/2016 ዓ.ም በቀጥታ ከ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ይተላለፋል ፡፡ የእለቱ ዳኞች ሙዚቀኛ የሺ ደምመላሽ ፣ ሙዚቀኛ ትዕግስት ሐይሉ (እግቱ) ፣ ዳነሰኛ እና ድምፃዊ ያሬድ ነጉ ይጠብቁዋችኃል ፡፡
* የሙዚቃ ድምጫ ጥቆማ በዚህ ሳምንት በየኔ ቫይብ…
– 1979 የወጣ አልበም በጥንድ ሆነው ሰርተው ከአበረከቱልን መሀል ቆየት ያለውን እንጠቁም አልበሙን ለ አራት ሆነው የተጫወቱት ነው ኩኩ ሰብስቤ ፣ አረጋኸኝ ወራሽ ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ ፣ እብስት ጥሩነህ ይገኙበታል፡፡ ሙዚቃ ሙሉ በሙሉ በሮሀ ባንድ የተቀናበረ ሲሆን በግጥሙን ይልማ ገብረዓብ በዜማው ደግሞ ታላቁ አበበ መለሰ ተሳትፈዋል፡፡ በውስጡ ወድዬ ፣ ሸጋ ባለጋሜ ፣ ማን እንደ አንቺ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል ፡፡
*የሳምንቱ አነጋጋሪው በሙዚቃው ጉዞ ክስተታዊ ፡፡
ልጓም ያልተበጀለት ለ ሮያሊቲ ክፍያ ጉዳይ መቋጫው እስከ ምን ይሁን ?
በአፍሪካ የመጀመርያ የሆነው እና ሀገር በቀሉ በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች የተበጀው የሮያሊቲ ክፍያ ሳምንታዊ አነጋጋሪ ጉዳዮች ከሆኑት መካከል አራት አመት ሙሉ ያለምንም እረፍት በድካም የተለፋበት የሮያሊት ( የሙዚቃ ክፍያ ጉዳይ ) ባሳለፍነው ሰኞ መጋቢት 9/2016 ዓ.ም ከቀኑ 3:00 – 7: 00 ካሳንቺስ በሚገኘው የኢትዮጵያ አዕምሮ ጥበቃ ባለስልጣን መስርያ ቤት የስብሰባ አራዳሽ ታላላቅ ሙዚቀኞች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የሚመለከታቸው ሰዎች በአዳራሹ ተገኝተው ስለ ሮያሊት የክፍያ አሰባሰብ የክፍፍል ሁኔታ ፣ የመብት ጥሰት በማስከበር ፣ የአዲስ መልክ ስለ ተደራጀው የህግ ድጋፍ እና አበይተ ነጥብ በመድረኩ አንስተዋል ተወያይተዋል ፡፡
የሮያሊት ክፍያ በተመለከተ ወደ ስምምነት ተደርሶ የመጨረሻ መቋጫ ከሁለት ወር በኃላ ለ አራት አመት የተለፋበት የሙዚቃ ክፍያ ይጀምራል ቢባልም የአዕምሮ ንብረት ጥበቃ ባለስልጣን በኩል ይንን መረጃ ውድቅ አርጓል ፡፡
ውድቅ ያደረገበት ምክንያት የኢትዮጲያ የሙዚቃ እና የቅጂ መብቶች የጋራ አስተዳደር የኢትዮጲያ ቅጂ ተዛማች መብቶች ማህበር የጋራ የሆነ የሮያሊቲ የሙዚቃ ክፍያ አስመልክተው ሙሉ አካሄዱን ለ ባለስልጣኑ ቀርቦ ሳይፀድቅ ምንም አይነት የሮያሊቲ ክፍያ የለም ምክንያቱም ሁለቱ ማህበራት አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ስር ናቸው ሲል ገልጿል ፡፡
ሮያቲክ ክፍያ ጉዳይ ስልሳ አንድ አመት በላይ በክርክር እንደ ቆየ የሚታወስ ሲሆን እና አሁን ደሞ በአራት አመት ውስጥ በታላቁ ኤልያስ መልካ በኩል ተቀስቅሷል በቀጣይ የሚከሰቱ ክስተታዊ ጉዳይ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት እየተከታተለ ያደርሳችኃል ፡፡
@biggrs @yenevibe