ንግድ ባንክ ቀነ ገደብ አስቀመጠ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም ችግር በገጠመው ወቅት ገንዘብ የወሰዱ ግለሰቦች እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ የማይመልሱ ከሆነ በሕግ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው አስታወቀ።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ለቢቢሲ ኒውስ ዴይ ሲናገሩ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ካልመለሱ ማንነታቸውን ለፖሊስ እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል።
“በዲጂታል ነው ዝውውር የፈጸሙት። ደንበኞቻችን ስለሆኑ እናውቃቸዋለን። የፈጸሙት ተግባር በሕግ ያስጠይቃቸዋል። ለፖሊስ ማንነታቸውን እናሳውቃለን” ብለዋል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ “አሁን የፈጸሙት የገንዘብ ዝውውር በመታወቁ የወሰዱትን ገንዘብ በራሳቸው እየመለሱ ያሉ አሉ” ብለዋል። በተፈጠረው ችግር ወቅት የማይገባቸውን ገንዘብ የወሰዱ ደንበኞቹ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ እንዲመልሱ የጠየቁት አቤ ሳኖ፤ ይህ ካልሆነ ግን ክስ ተመስርቶ ግለሰቦቹን ማንነት ለፖሊስ አሳልፎ እንደሚሰጥ አስጠንቅቀዋል።
ማንነታቸውን ለፖሊስ አሳልፋችሁ መስጠታችሁ ከደንበኞቻችሁ ጋር ያላችሁን ግንኙነት አያበላሽባችሁም ወይ ተብለው የተጠየቁት አቤ ሳኖ፤ “ከሌቦች ጋር ስለምን ዓይነት ግንኙነት ነው የምናወራው?” ብለው ጠይቀው፤ “በሂሳባቸው የሌላቸውን ገንዘብ ነው የወሰዱት። የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ እንደወሰዱ በጣም እርግጠኛ ነን” ሲሉ መልሰዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
@yenevibe