ለ90 መምህራን በብድር የኤሌክትሪክ መኪና ተበረከተ።
ጤግሮስ ትሬዲንግ ከፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማኀበር ጋር በመሆን ዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተከናወነ መርሐግብር ለ90 መምህራን በብድር የኤሌክትሪክ መኪና ተበረከተ።
የጤግሮስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሐኔ ጌታቸው እንደገለጹት የአባልነት መስፈርታቸውን ላሟሉ እና ቁጠባቸውን ለአጠናቀቁ 90 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የመጀመሪያ ዙር ዘመናዊ የኤሌትሪክ መኪኖች ብድር የመስጠት ፕሮጀክት ከፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስ/ማኅበር እንዲሁም ከበላይነህ ክንዴ ጄነራል ትሬዲንግ ጋር በተደረገ ስምምነት መስጠት እንደተጀመረ ገልጸዋል።
“የእውቀት ባለቤት ውለታ እንመልስ” በሚል መሪ ቃል ለሀገር ባለውለታ ለሆኑ መምህራን ቁጠባና ብድርን መሰረት ያደረገ “ደራሽ” የተሰኘ የኤሌክትሪክ መኪና ግዥ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐግብር ላይ 90 ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች በበላይነህ ክንዴ የመኪና መገጣጠሚያ የተመረቱ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ቁልፍ ተበርክተዋል።
በቀጣይ የጤና ፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የኪነጥበብ ባለሙያዎችን የመኪና እና የቤት አቅርቦትን በብድር ተደራሽ ለማድረግ ዝርዝር ጥናቶች እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት
የጤግሮስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሐኔ ጌታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ስራ እንዲሰራ ለአገዙ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።