የሮያሊቲ ጉዳይ ወደ ፍፃሜ ተቃርቧልከሁለት ወር በኋላ በአዲስ አበባ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ለሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ክፍያ እን…

Reading Time: < 1 minute
*

የሮያሊቲ ጉዳይ ወደ ፍፃሜ ተቃርቧል

ከሁለት ወር በኋላ በአዲስ አበባ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ለሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ክፍያ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ተባለ::

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች የላባችን ፍሬ ያሉትን የሮያሊቲ ክፍያ ለማስጀመር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል::

የኢትዮጵያ የሙዚቃና የቅጂ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የሙዚቃ ዘርፍ ማህበር ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ እንዳለው ከሁለት ወር በኋላ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሮያሊቲ ክፍያን በፌደራል ደረጃ መሰብሰብ እንደሚጀምር ገልፆል።

የሙዚቃው ዘርፍ የፈጠራ መብት ተካፋዮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ በ2009 ዓም በአዋጅ የፀደቀውን ህግ ለማስፈፀም ባለፉት አራት አመታት በርካታ ውጣ ውረጆችን አልፈን እዚህ ደርሰናል ያሉት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጂና ዘርፍ ማህበሩ ፕሬዝዳንት የክብር ዶ/ር አርቲስት ዳዊት ይፍሩ፤ አሁን ወደመጨረሻው ተቃርበናል ብለዋል።

“የሮያሊቲ ጉዳይ መሳካት የኤሊያስ መልካ ሐውልት ነው።” ያሉት ደግሞ የአ/አ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ሃላፊው አቶ ሰርፀፍሬ ስብሃት ናቸው። አክለውም የኪነጥበብ ባለሙያውን ሸክም ለማቅለል የሮያሊቲ ክፍያ እና የኪነጥበብ ኢንቨስትመንት ኮድ መኖሩ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

“በጥቂት ሰዎች ትግልና ትጋት እዚህ ደርሶ ማየቴ እጅግ ደስ አሰኝቶኛል።” የሚለው የኢትዮጵያ የሙዚቃ የቅጂና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር የቦርድ ሰብሳቢው ድምፃዊ ሐይሌ ሩት ነው። ማህበሩ በአስተዳደር፣ በሕግ ባለሙያዎች እና በቴክኖሎጂ ሰዎች ተደግፎ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ የሮያሊቲ ክፍያን በፌዴራል ደረጃ ከሚገኙ መገናኛ ብዙሃን እንደሚጀምር ገልፆ፤ በቀጣይም ከሆቴሎች (መዝናኛ ስፍረዎች) እና በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የሬዲዮና የቲቪ ጣቢያዎች ተግባራዊነቱ እንደሚታይ ጠቁሟል።

@yenevibe
81820cookie-checkየሮያሊቲ ጉዳይ ወደ ፍፃሜ ተቃርቧልከሁለት ወር በኋላ በአዲስ አበባ የሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ለሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ክፍያ እን…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE