አለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ሽልማት ያገኘው የጀርመን ሪልእስቴት የሆነው ሮክስቶን ኢትዮጵያ ተወዳጇን እና ሁለገቧን ተዋናይት እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ተሟጋች አርቲስት አምለሰት ሙጬን የከፍታ አፓርትመንቶች ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን ዛሬ ጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም በሀያት ሪልስቴት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳወቀ።
አርቲስት አምለሰት ሙጬ የሮክስቶን ኢትዮጵያ ሪል ስቴት ብራንድ አምባሳደር የተመረጠችበት ዋነኛው ምክንያት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሮክስቶን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድያምሰገድ ኢያሱ እንደገለጹት አረንጓዴ ዓለምን ለመፍጠር በሚደረጉ ሁለንተናዊ ተሳትፎዎች ላይ እውቅናዋን ተጠቅማ የተለያዩ ንቅናቄዎችን ማሳካት በመቻሏ እና ባላት ግላዊ የማንነት ጠባይ፣ ቁርጠኝነት እንዲሁም ያሏት ትልልቅ ራእዮች በሙሉ ድምጽ እንድትመረጥ አድርጓታል ብለዋል።
አርቲስት አምለሰት ሙጬ በበኩሏ አምባሳደር ሆና በመመረጧ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጠችው መግለጫ ላይ አንደአብራራችው ዘላቂነት ካለው የሪልእስቴት ልማት ኩባንያ ጋር አብሬ በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ብላለች ።
በቀጣይ አርቲስት አምለሰት ሙጬ በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮ፣ በተለያዩ የህትመት እና የዲጂታል የማስታወቂያ አማራጮች ላይ የከፍታን መኖሪያ አፓርታማዎችን፣ አገልግሎቶችን እና የአኗኗር ዘይቤዎችን በብቃት የምታስተዋውቅ ይሆናል።
የሮክስቶን ዋና ስራ አስፈፃሚ መስራች ሚስተር ዲትሪክ አሮጄ እንደገለጹት አዲስ አበባ ሲግናል አካባቢ ” ከፍታ አፖርትመንት” በሚል ስያሜ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ እያስገነባ የሚገኘው ግዙፍ ህንጻ 16 ወለል ያለው ሲሆን በቂ የመኪና ማቆሚያ ጨምሮ ዘመኑ የደረሠበት ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ተገልጿል።
ሮክስቶን በጀርመን፣ በስፔን እና በፖርቹጋል ፕሮጀክቶችን የገነባ እና በአውሮፓ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በማስረከብ ከፍተኛ ልምድ ያካበተ የሪል እስቴት ድርጅት ሲሆን ሮከስቶን ኢትዮጵያ ሪል ስቴት ከአምስት አመት በፊት በምስራቅ አፍሪካ አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጅዎች ለማስተዋወቅ እና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የተለያዩ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችለውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።
632210cookie-checkአርቲስት አምለሰት ሙጬ የሮክስቶን ኢትዮጵያ ሪል ስቴት ብራንድ አምባሳደር ሆነች።no
አርቲስት አምለሰት ሙጬ የሮክስቶን ኢትዮጵያ ሪል ስቴት ብራንድ አምባሳደር የተመረጠችበት ዋነኛው ምክንያት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሮክስቶን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አድያምሰገድ ኢያሱ እንደገለጹት አረንጓዴ ዓለምን ለመፍጠር በሚደረጉ ሁለንተናዊ ተሳትፎዎች ላይ እውቅናዋን ተጠቅማ የተለያዩ ንቅናቄዎችን ማሳካት በመቻሏ እና ባላት ግላዊ የማንነት ጠባይ፣ ቁርጠኝነት እንዲሁም ያሏት ትልልቅ ራእዮች በሙሉ ድምጽ እንድትመረጥ አድርጓታል ብለዋል።
አርቲስት አምለሰት ሙጬ በበኩሏ አምባሳደር ሆና በመመረጧ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጠችው መግለጫ ላይ አንደአብራራችው ዘላቂነት ካለው የሪልእስቴት ልማት ኩባንያ ጋር አብሬ በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ ብላለች ።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
የሮክስቶን ዋና ስራ አስፈፃሚ መስራች ሚስተር ዲትሪክ አሮጄ እንደገለጹት አዲስ አበባ ሲግናል አካባቢ ” ከፍታ አፖርትመንት” በሚል ስያሜ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ እያስገነባ የሚገኘው ግዙፍ ህንጻ 16 ወለል ያለው ሲሆን በቂ የመኪና ማቆሚያ ጨምሮ ዘመኑ የደረሠበት ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ተገልጿል።
ሮክስቶን በጀርመን፣ በስፔን እና በፖርቹጋል ፕሮጀክቶችን የገነባ እና በአውሮፓ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በማስረከብ ከፍተኛ ልምድ ያካበተ የሪል እስቴት ድርጅት ሲሆን ሮከስቶን ኢትዮጵያ ሪል ስቴት ከአምስት አመት በፊት በምስራቅ አፍሪካ አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጅዎች ለማስተዋወቅ እና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የተለያዩ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት የሚያስችለውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ