የአስቻለው ፈጠነ አልበም ነገ ይለቀቃል

Reading Time: < 1 minute
በ”እናትዋ ጎንደር” እና “ካሲናው ጎጃም” በተሰኙት ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ “አስቻለ” የተሰኛውን የሙዚቃ አልበም ነገ ጥር 3 ቀን 2016ዓ.ም አርብ ማታ በቡርቧክስ ሬከርድስ ዩቱዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ድምጻዊው በዛሬው እለት በቤስት ዌስተርን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቋል።

ድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ በመግለጫው ላይ እንደተናገረው የሙዚቃ አልበም ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ ትግርኛን፣ ኦሮምኛን ፣የጉምዝ እና አገወኛ ቋንቋን የያዘ ሲሆን ይህ ስራ እንዲሳካ ላደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች ምስጋናውን አቅርቧል።

ድምፃዊ ፣ የዜማ ፣ ግጥም ፣ ደራሲ እና የክራር ተጫዋች አስቻለው ፈጠነ ከሰራቸው ትራኮች መካከል ዘጠኙ በቅርቡ በሞት የተለየው ለአቀናባሪ እና ለሙዚቃ ባለሙያው ለነበረው ለእስራኤል መስፍን መታሰቢያ ይሆናል ተብላል።

ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ባህላዊ መሳሪያዎችን በአልበሙ እንደተጠቀመ የተገለፀ ሲሆን ከ20 በላይ አጃቢዎችም እንደተካተቱበት ተጠቁሟል፡፡

62950cookie-checkየአስቻለው ፈጠነ አልበም ነገ ይለቀቃል

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE