ሀገር አቀፍ የኀብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጓል።

Reading Time: 2 minutes
የኅብረት ሥራ ማኅበራት በግብርና፣ በቁጠባና ብድር፣ በኢንቨስትመንት መስክ የሚጫወቱትን ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ነው የተባለለት ሪፎርም ትናንት ታህሳስ 26 ቀን 2016ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ይፋ ተደርጓል።

በሪፎርሙ ይፋ ማድረጊያ መርሐግብር ላይ የግብርና ሚኒስቴር ዶክተር ግርማ አመንቴ ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ በዚሁ መርሐግብር ጊዜላይ ተገኝተው እንደገለጹት፤ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ ግብዓቶች በማቅረብ አምራቹ ባመረተው ልክ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ በኩል አበረታች ጅምሮች አሉ።
እንዲያም ሆኖ ቴክኖሎጂዎችን በጥራትና በብዛት ማቅረብና ገበያን መረጋጋት አሁንም የበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

ኅብረት ሥራ ማኅበራት ሁሉን አቀፍ ለውጥ እንዲያመጡ በመስኩ የለውጥ ሥራዎችን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ሚኒቴሩም በዚህ ረገድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ማህበራትን ለማጠናከር እንዲሁም የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል 50 ቢሊየን ብር በቁጠባና በዕጣ ማሰባሰብ ተችሏል።

በዚህም ለአርሶና አርብቶ አደሩ በአማካይ በዓመት 12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ብድር እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም በመስኩ እየገጠመ ያለውን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ረገድ ወሳኝ ድርሻ እየተጫወተ ነው ብለዋል።

የኅብረት ሥራ ማኅበራቱ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ፣ በድርቅ የተጎዱ ወገኖችና እንዲሁም የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ ወገናዊ ግዴታቸውን እየተወጡ መሆኑን አብራርተዋል።

ኅብረት ሥራ ማኅበራት በግብርና ግብዓት፣ በቴክኖሎጂ ቅርቦት፣ በምርት ገበያ እሴት መጨመርና መሰረተ ልማት አቅርቦት ላይ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ርብርብ ይደረጋል ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት በገጠርና በከተማ ከ28 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አባላት ያሏቸው ከ110 ሺህ በላይ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንደሚገኙ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

403 ዩኒየኖች እንዲሁም 5 ፌዴሬሽኖች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ኅብረት ሥራ ማኅበራቱ በግብርና፣ በሸማቾች፣ በቁጠባና ብድር እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ተደራጅተው ከ49 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ማፍራት መቻላቸውም እንዲሁ።

62890cookie-checkሀገር አቀፍ የኀብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጓል።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE