ለልደት በዓል 70 ተጓዦች ወደ እስራኤል ሊያቀኑ መሆኑን ተገለጸ።

Reading Time: 2 minutes
በብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም ሃገረ ስብከቶች ሊቀ-ጳጳስ የተመራውና በቅርቡ ወደ እስራኤል አገር የተጓዘው የልዩ ሚሽን የእስራኤል ልዑክ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ መመለሱን እና ሁለተኛው ዙር ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።

በእስራኤልና በፍልስጤም የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ፣ አሁን ላይ በእስራኤል ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን እና ተጓዦች ስጋት እንዳይገባቸው በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቶ አለኸኝ አድማሱ በጋዜጣዊው መግለጫ መርሐግብር ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን አስተላልፏል።

የመጀመሪያውን ዙር የጉዞ ግብዣና የውይይት መድረኮችን ያዘጋጀውና ያመቻቸው ተቀማጭነቱ በሀገረ እስራኤል የሆነው « ቬሬድ ሃሻሮን ጉዞና አስጎብኚ» ሲሆን በኢየሩሳሌምና አካባቢዋ እንዲሁም በፍልስጤም አስተዳደር እና በመላው እስራኤል የሚገኙ ቅዱሳን እና ታሪካዊ ሥፍራዎች በማስጎብኘት ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረ ድርጅት መሆኑን በምስረታ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ሃይማኖታዊ ጉዞ አዘጋጅ ድርጅቶች ማህበር ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2016ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል።

ማህበሩ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን በመጀመሪያ በተከናወነው ጉዞ ላይ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ጨምሮ የአስጎቢኚ የጉዞ ማኀበራት አመራሮች እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ የሚገኙ መካነ ቅዱሳን ጨምሮ ጎልጎታ፣ ቀራኒዮ፣ የኢትዮጵያው የዴር ሱልጣን ገዳም፣ የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ጨምሮ ልዩ ልዩ ቅዱሳንና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዲሁም ታላላቅ እና ዋና ዋና የእስራኤል ሙዚየሞችን መጎብኘት መቻሉን ገልጸዋል።

ሁለተኛው ዙር ለልደት በዓል ወደ እስራኤል የሚጓዘው ልዑክ የፊታችን አርብ ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የሚጓዝ ሲሆን በዚህ ጉዞ ላይ ከ70 በላይ ተጓዦች ለጉዞ ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ሃይማኖታዊ ጉዞ አዘጋጅ ድርጅቶች ማህበር ገልጸዋል።

62870cookie-checkለልደት በዓል 70 ተጓዦች ወደ እስራኤል ሊያቀኑ መሆኑን ተገለጸ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE