3ኢ ኤቨንትስ ከተለያዪ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት “የኢድ ዋዜማዎች በሚሊኒየም ” በሚል መሪ ቃል ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ. ም የኢድ ዋዜማ መሰናዶዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በሚደረገው የኢድ ኤክስፖ እና ባዛር
ከ200 በላይ አምራችና ነጋዴዎች እና ከ 300,000 በላይ ጎብኚዎች የሚሳተፉበት ሲሆን ዝግጅቱም የሚካሄደው በሚሊኒየም አዳራሽ ዉስጥ የሚዘጋጅ ሲሆን በዚህ ዝግጅት ላይ የህጻናት እና የአዋቂዎች የተለያዩ አልባሳትና ተዛማጅ እቃዎች መገበያያ፣ ልዩ የማፍጠሪያ የምግብ አይነቶች እና የሃላል መጠጥ መሸጫ፣ ኢትዮጵያ በኢስላም ታሪከ ውስጥ ያላትን ታሪከ በጉልህ የሚያሳዩ ቅርሶች የሚጎበኙበት ስፍራ፣ ግብይት ሲፈጽሙ በዛውም የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የሚሳተፉበትን አጋጣሚ ከመፍጠሩም በተጨማሪ የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ ውድድሮች እና ትዕይንቶች የሚካሄዱበት መድረከ ሲሆን ለልጆች ምቹ የመጫወቻ ቦታ እና ፈርድ እና ተራዊህ ሰላትን ጨምሮ መስገድ የሚቻልበት ሰፊ ቦታ ያጠቃለለ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
በዚህ መርሐግብር ላይ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሚዲያ አካላት በርካታ ጎብኚዎች የሚሳተፉበት፣ በሃገር ዉስጥ ያሉ ባለሃብቶች፣ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ጎብኚዎች የሚሳተፉበት የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚሰሩበት እና ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ ለደንበኞቻቸው ተደራሽ የሚያደርጉበት ደማቅና ሰፊ መድረከ እንደሚሆን አዘጋጀ 3ኢ ኤቨንትስ በሰጠው መግለጫ ላይ አብራርተዋል።
627110cookie-checkኢትዮ ኢድ ኤክስፖ እና ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው።no