የየሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ አዘጋጅ ያሜንት ኢቬንትስ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።

Reading Time: < 1 minute
በያሜንት በኩል የየሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ አዘጋጅ ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፕሬዚዳንት አስናቀ አማኑኤል፣ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በኩል ደግሞ የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

የሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ የሚያዘጋጀው የጋብቻ ሥነ ስርዓት እንደ ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ፕሮጀክት እንዲዘልቅና የህዝብ ለህዝብ ትስስርንና መተማመን እንዲጠናከር ብሎም የሀገሪቷን የቱሪስት መስህብ ዕድሎችን በማስፋፋት ረገድ ሥምምነቱ የጎላ እንደሚሆን ተገልጿል።

200 ሙሽሮች በልዩ ልዩ ኢትዮጵያዊ የባህል አልባሳትና ማጌጫዎች ተውበው የሚጋቡበት የሺህ ጋብቻ ላይ ልማቶችን ለማስተዋወቅ፣ የአለም አቀፋዊ ቱሪስቶችን ትኩረት ለመሳብ የሚችሉ ማህበራዊና ባህላዊ ትዕይንቶች የሚቀርቡ በመሆናቸው፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት የሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥራል ተብሏል።

በጥር ወር መጀመሪያ የሚካሄደው የሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ 2016 ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

62670cookie-checkየየሺህ ጋብቻ ካርኒቫልና ኤክስፖ አዘጋጅ ያሜንት ኢቬንትስ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE