ላዳ ታክሲዎች በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች መቀየር ተጀመረ !

Reading Time: 2 minutes
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር  በአዲስ አበባ ለረዥም ጊዜ የታክሲ አገልግሎት የሠጡትን ላዳ ተሽከርካሪዎችን በዘመናዊ መኪናዎች በመቀየር ለባለንብረቶቹ ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2016ዓ.ም ፒያሳ ጊዮርጊስ አካባቢ በሚገኘው በህብረት ስራ ማህበር ዋና መስሪያ ቤት  አስረከበ።

«ህብረት ለስምረት» በሚል መሪ ቃሉ የሚታወቀው
አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለሶስተኛ ዙር 17 ለሚሆኑ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች አዲስ የሆኑ  እና ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች በ30 በመቶ ቅድመ ክፍያ በሶስት ወራት ውስጥ በብድር አማራጭ መስጠቱን የተቋሙ የኮርፖሬት ሴልስ ዲፓርትመን ሄድ ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው በኃይሉ  የገለጹ ሲሆን በሶስቱም ዙር 42 ለሚሆኑ አሽከርካሪዎች በአዲስ መኪና መቀየራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ገልጸዋል።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 147/91 እና ይሄንን አዋጅ ለማሻሻል በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 402/96 መሰረት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ነዉ።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በዘጠኝ ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ጀምሮ አሁን ላይ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊየን ብር  በላይ ካፒታል መድረሱን አቶ እንዳልካቸው በኃይሉ ተናግረው መጭውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ቁጠባ  ለተለያዩ አላማዎች የሚውል ብድር እስከ በዓሉ  ዋዜማ ድረስ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ማህበሩ ላለፋት አስራ አንድ አመታት ከሰባት ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ እንዲሁም ለሶስት ሺህ ያህል ሰዎች የብድር አገልግሎትን በመስጠት በርካቶች ስራቸውን እንዲያስፋፉ እና ስራ እንዲፈጥሩ እንዲሁም ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸዉን ወደተሻለ ህይወት እንዲቀይሩ እየሰራ ይገኛል።

62650cookie-checkላዳ ታክሲዎች በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች መቀየር ተጀመረ !

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE