ፀደይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ አስጀመረ ።

Reading Time: < 1 minute
ፀደይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ የመተግበሪያና እና USSD አገልግሎት መጀመሩን በዛሬው እለት በሸራተን ሆቴል ባካሄደው የአገልግሎት ማስጀመሪያ የምረቃ በዓል ላይ አስታውቋል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ መኮንን የለውምወሰን እንደገለጹት ባንኪንግ አገልግሎቶች ምቹ፣ ተደራሽነት፣ ወጪ ቆጣቢ፣ የተሻሻለ ደህንነት እና ተጨማሪ የፋይናንስ አስተዳደር መሳሪያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚሰጡ ሲሆን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው በማንኛውም ቦታ ከኢንተርኔት ውጭ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ፀደይ ባንክ በአሁኑ ሰዓት ካፒታሉ 12 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ ሃብቱ ከ55 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሻገሩን የባንኩ መረጃ ያመላክታል።

በ1988 ዓ.ም የገጠር ብድር አገልግሎት በሚል ስራ የጀመረ ሲሆን በ1989 ዓ.ም አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በመሆን በአማራ ክልል በ10 ዞኖች ወደ ማይክሮፋይናስ ተቋም በማሳደግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከ12ሺህ 600 በላይ ሠራተኞች እና ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያቀፈ ባንክ መሆን ችሏል።

62460cookie-checkፀደይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ አስጀመረ ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE