ኤቫ ሌግዤሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የፊታችን ታህሳስ 13 እና 14 2016ዓ.ም በጊዮን ሆቴል “ፌሽታ” የተሰኘ የሕፃናትና የወጣቶች ፌስቲቫል ሊካሄድ መሆኑን አዘጋጆቹ በሳፋየር አዲስ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አብራርተዋል።
በመርሐግብሩ ላይ የሕፃናት እና ወጣቶች ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች ፣ የስጦታ ዕቃ አስመጪና ሻጮች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢዎች ፣ የመዝናኛ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።
ከዚህም በተጨማሪም የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች፣ ጌም ዞኖች ፣ የሰርከስ ትርሲት ፣ ባህላዊ ዘመናዊ የሙዚቃ ዝግጅት እንዲሁም የተለያዩ የጨዋታ ውድድሮች ይካሄዳሉ።
በዕለቱ መግቢያው 250 ብር ሲሆን ቲኬቱን ከነገ ታህሳስ 6 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ በቴሌብር ላይ እንደሚሸጥ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
(ጌች ሐበሻ)
624000cookie-check“ፌሽታ” የተሰኘ የሕፃናትና የወጣቶች ፌስቲቫል በቀጣይ ሳምንት ሊከናወን ነው።no