ገናን በሚሊኒየም የገና ባዛር እና ኤክስፖ ከታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ በዛሬው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ይህ ኤግዚቢሽን የተለያዩ የመዝናኛ የምግብ እና የመጠጥ ፕሮግራሞች የሚገኙበት ባዛር እና ኤክስፖ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የፊታችን ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጠናት፣ ባለሀብቶች እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት በይፋ እንደሚከፈት ተገልጿል፡፡
በዝግጅቱም ላይ አልባሳት፣የስጦታ እቃዎች አቅራቢና አስመጪ፣ የምግብና መጠጥ ሻጮች ፣ የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በአጠቃላይ ከ2000 በላይ አስመጪና ሻጮች የሚሳተፉበት ሲሆን በዚህም ዝግጅት በቀን ከሰባት ሺህ 7,000 እስከ 10,000 ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህም በተጨማሪ በየቀኑ በሀገራችን የሚገኙ ባህላዊ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ባለሙያዎች በየቀኑ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ በሀገራችን የተለያዩ ሁነቶችን (ኤቨንቶችን) በማዘጋጀት ሕጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ሲሆን ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አመታዊ በዓላት እና ሀገር አቀፍ ቀናትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኢግዚቢሽን እና ባዛሮችን እንዲሁም የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጅ ድርጅት ነው፡፡
623800cookie-checkገናን በሚሊኒየም የገና ባዛር እና ኤክስፖ ከታህሳስ 11 እስከ ታህሳስ 27 ይካሄዳልno
ይህ ኤግዚቢሽን የተለያዩ የመዝናኛ የምግብ እና የመጠጥ ፕሮግራሞች የሚገኙበት ባዛር እና ኤክስፖ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የፊታችን ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጠናት፣ ባለሀብቶች እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት በይፋ እንደሚከፈት ተገልጿል፡፡
በዝግጅቱም ላይ አልባሳት፣የስጦታ እቃዎች አቅራቢና አስመጪ፣ የምግብና መጠጥ ሻጮች ፣ የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በአጠቃላይ ከ2000 በላይ አስመጪና ሻጮች የሚሳተፉበት ሲሆን በዚህም ዝግጅት በቀን ከሰባት ሺህ 7,000 እስከ 10,000 ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ በሀገራችን የተለያዩ ሁነቶችን (ኤቨንቶችን) በማዘጋጀት ሕጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ሲሆን ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አመታዊ በዓላት እና ሀገር አቀፍ ቀናትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኢግዚቢሽን እና ባዛሮችን እንዲሁም የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጅ ድርጅት ነው፡፡
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ