ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የፊታችን ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በገና በዓል ዋዜማ ለአምስት ሺህ የቤት ቆጣቢ ባለዕድለኞች ዕጣ የማውጣት ሥነሥርዓት እንደሚከናወን አሳወቁ።
የእጣ አወጣጥ ስነስርአት እጅግ በጥንቃቄ እና ሀላፊነት በተሞላበት፣ ተጠያቂነት በሰፈነበት መንገድ እንዲካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በተለይ ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ጋር በመቀናጀት መሠራቱን የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ ገልጸዋል።
የምዝገባ ሂደቱ ህዳር 30 ቀን 2016ዓ.ም የነበረ ቢሆንም በቤት ፈላጊዎች ጥያቄ መሰረት እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ የቤት ምዝገባው እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
ኤዜድ ሪል እስቴት ፣ላመስግን ውበቱ አፖርትመንት፣ራስ ሪል ስቴት እና ቱዋይ ኢንጅነሪንግ ጋር በጋራ በመሆን በቀጣይ አንድ አመት 100 መቶ ቤቶችን በመገንባት አነስተኛ እና ለመካከለኛ ገቢ ላላቸው የቤት ፈላጊዎች ለማስረከብ ከኪሀውሲንግ ጋር የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።