ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ባቋቋመው ዘመናዊ የምግብ ማቀነባበሪያ ኮምፕሌክስ እማካይነት “ኤስ” (ACE) በሚል ብራንድ የታሽጉ ጣፋጭ ኬክ ምግቦችን እያመረተ በመላው ኢትዮጵያ ባሉት ወኪሎች አማካኝነት እያከፋፈለ ሲገኝ ድርጅቱ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ በምርት አቅርቦትና በገቢ ግብር በኢኮኖሚው ውስጥ የድርሻውን አስተዋፅአ እያበረከተ ይገኛል።
ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኤስ (ACE) ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማስፋት የሚያስችልና ከስድስት ወር እስከ አንድ-አመት የሚዘልቅ የ’ኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን” እቅድ አውጥቶ ለመተግበር ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን ለዚህም 50 ሚሊዮን ብር መመደብን እና አርቲስት ሀናን ታሪክ ደግሞ የድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ምርት ለማስተዋወቅ በ10 ሚሊዮን ብር ለቀጣይ ሁለት አመት ብራንድ አምባሳደርነት ሹመት መሠጠቱን በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
በቻይና አገር ታዋቂ የምግብ አምራች ኩባንያ የሆነው ኤስ(ACE)፤ የተመሰረተው እኤአ በ 1979 ነው፡፡ ኩባንያው ባለው የዳበረ የኢንዱስትሪ ልምድ እና ሰፊ የምርቶች ስብጥር በአለም አቀፍ የገበያ ስርአት ውስጥም ቢሆን በጣም የታወቀ ተቋም ነው። ኩባንያው ትኩረት አድርጎ የሚያመርታቸው እንደ ኩኪስ፤ ካንዲስ እና ቾኮሌት ያሉ ጣፋጩ ምግቦችን ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ በተለይም “ካስተርድ ፓይ” የተባለው ከፍ ያለ የኮኮብ ማእረግ ስም ካላቸው ምርቶቻችን መካከል አንዱ ነው።
ካለፈው አመት ጀምሮ ኩባንያችን ኤስ(ACE) በአፍሪካ ገበያ በንቃት እየተስፋፋ የመጣ ሲሆን፤ ላቅ ያሉ የማምረቻ ማእከሎችንም በኢትዮጵያ፤ በናይጄሪያ፤ ኮትዲቮር፣ ስኔጋል፤ ታንዛኒያና በሌሎችም ቦታዎች አቋቁሟል፤ ይህም በአካባቢው ገበያ ውስጥ በጥንካሬ እንደሚገኝ ተገልጿል።
622300cookie-checkአርቲስት ሀናን ታሪክ የድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ምርት ለማስተዋወቅ በ10 ሚሊዮን ብር ፈረመች።no
ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ኤስ (ACE) ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማስፋት የሚያስችልና ከስድስት ወር እስከ አንድ-አመት የሚዘልቅ የ’ኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን” እቅድ አውጥቶ ለመተግበር ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን ለዚህም 50 ሚሊዮን ብር መመደብን እና አርቲስት ሀናን ታሪክ ደግሞ የድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ምርት ለማስተዋወቅ በ10 ሚሊዮን ብር ለቀጣይ ሁለት አመት ብራንድ አምባሳደርነት ሹመት መሠጠቱን በዛሬው እለት በስካይ ላይት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
በቻይና አገር ታዋቂ የምግብ አምራች ኩባንያ የሆነው ኤስ(ACE)፤ የተመሰረተው እኤአ በ 1979 ነው፡፡ ኩባንያው ባለው የዳበረ የኢንዱስትሪ ልምድ እና ሰፊ የምርቶች ስብጥር በአለም አቀፍ የገበያ ስርአት ውስጥም ቢሆን በጣም የታወቀ ተቋም ነው። ኩባንያው ትኩረት አድርጎ የሚያመርታቸው እንደ ኩኪስ፤ ካንዲስ እና ቾኮሌት ያሉ ጣፋጩ ምግቦችን ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ በተለይም “ካስተርድ ፓይ” የተባለው ከፍ ያለ የኮኮብ ማእረግ ስም ካላቸው ምርቶቻችን መካከል አንዱ ነው።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ