ኢቢ የስ ፈርኒቸር «አሮጌን በዓዲስ»የተሰኘ አዲሱን ምርቱን አስተዋወቀ።

Reading Time: < 1 minute
የቲክቶክ ፈርጡንም ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መረጧል

አስር አመቱን የሚያከብረው ኢቢየስ ፈርኒቸር ሊስትሮ እቃዎችን በነፃ ለወጣቶች ለመስጠት መዘጋጀቱን አሳውቋል።

ኢቢ የስ ፈርኒቸር አሮጌን በአዲስ የተሰኘ አዲሱን ምርቱን እንዲሁም ብራንድ አምባሳደሩን አስተዋወቀ።

ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ደንበል ጋዜቦ አካባቢ በሌበንዝ ታወር በሚገኘው ሾው ሩሙ የአስር አመት የስኬት ጉዞውን በማስመልከት ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች እና የሚድያ ባለሙያዎች የአስር አመት ጉዞውን አስመልክቶ አሮጌን በአዲስ የተሰኘ በሽያጩም ላይ  10 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን እንዲሁም ማህበራዊ ሀላፊነቱን ሊስትሮ ለሚያስፈልጋቸው ልጆች አስፈላጊውን እገዛ ሊያደርግ ሙሉ መሰናዶውን ማጠናቀቁን የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድማገኘሁ ደምሴ ገልፀዋል።

በማህበራዊ ሚድያው ከሰባት መቶ ሀምሳ መቶ ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ማህበራዊ ሚድያው ላይ በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው ብሩክ ዘሪሁን(ብሩክ ዚቲ) ጥሩ ዘር በመዝራት የተሻለ ስራዎችን ከኢቢ የስ ፈርኒቸር ጋር ለቀጣዮቹ አመታት በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ኢብየስ ፈርኒቸር መርጦኝ አብሮኝ ለመስራት ስለወሰነ ከልብ አመሰግናለሁ ሲል አምባሳደሩ ምስጋናውን ለተቋሙ አቅርቧል።

ለቀጣዮቹ አመታት ለብራንድ አምባሳደርነቱ በሚልየኖች እንደተከፈለው የማርኬቲንግ ሀላፊው አስታውቀዋል

ኢቢ የስ ፈርኒቸር ባለፋት አስር አመታት አብረውት የሰሩ ተቋማትን አመስግኗል።

62210cookie-checkኢቢ የስ ፈርኒቸር «አሮጌን በዓዲስ»የተሰኘ አዲሱን ምርቱን አስተዋወቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE