???? አዲስ አበባ በሚገኙ በ149 የትምህርት ቤት አዳራሾች የስፖርት ስልጠናዎች ሊጀመር ነው።
ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ ከኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ፌደሬሽኖች በተገኙበት በዛሬው እለት አራት ኪሎ በሚገኘው ወወክማ አዳራሽ የጋራ ውይይትና ምክክር አካሂደዋል።
ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ ከኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር በ298 ትምህርት ቤቶች በ149 የትምህርት ቤት አዳራሾች የስፖርት ስልጠናዎች ሊጀምር አንደሆነ እና ይህንንም ስራ ሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ አሰልጣኞችን በመመደብ ስልጠናው በመስጠት፣ ውድድሮችን በማዘጋጀት እንዲሁም ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር በትምህርት ቤት ያሉ አዳራሾችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ በማዘጋጀት በጋራ እንደሚሰሩ ተገልጿል።
ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር “ትምህርት ለትውልድ” በሚል ወጣቱን ከተለያዪ ሱስ እና አልባሌ ነገሮች ነፃ ለማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባ በተለያዪ ክ/ከተሞች በሚገኙ ት/ቤቶች ላይም እየሰራየሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ የግል ድርጅት ነው።
የዛሬው ውይይትና ምክክር ዋነኛ አላማ ሁሉም የቴኳንዶ፣ የማርሻል አርት ባለሙያዎች በጋራ ሆነው እየተመካከሩ በመስራት ይህን የእስፖርት ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት በማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን ማስቻል እንደሆነም ተገልጿል።
ኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከተመሰረተ 3 አመት እንደሆነው የተገለፀ ሲሆን በተለያዪ በጎ ስራዎች ላይ የሚሳተፍ ድርጅት ነው::
620200cookie-checkሌጀንድ ኢንተርናሽናል ፕሮ ቴኳንዶ ከኤሴቅ ዲኮር እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር የሥራ ማስጀመሪያ ውይይት አካሄደ።no