ከ265,000 ዶላር በላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

Reading Time: 2 minutes
በአርቲስት ታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብት ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ከ265,000 ዶላር በላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ቀደም ሲል በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በንቃት ሲሳተፍ የምናውቀው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የመሠረተው ግሎባል አልያንስ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኮሙዩኒቲ ባሰባሰበው ገንዘብ እና እምወድሽ ፋውንዴሽን ያበረከተለትን የህክምና መርጃ ቁሳቁስ ለጎንደር ዩኒቨርስቲ በዛሬ እለት አስረክቧል።

ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና መርጃ ቁሳቁሶችን በዛሬው ዕለት ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በተወካዮቹ አማካኝነት በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ድርጅት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ዶ/ር አስራት አጸደወይን በተገኙበት እርክክብ ተደርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን ይህን ትልቅ ድጋፍ ያደረጋችሁልን በወሳኝና በአስፈላጊ ሰአት ነውና ያገዛችሁንን በሙሉ ከልብ እናመሠግናለን ብለዋል።

የግሎባል አሊያንስ መስራቹ ታማኝ በየነም በመወከል ንግግር ያደረጉት ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ “ግሎባል አልያንስ ለኢትዮጵያውያን መበት የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ በሚያጋጥሙ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያግዙ የተለያዩ ጠንካራ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግመቆየቱን አውስተው
ግሎባል አልያንስ በመላው ኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘናት ያልደረሰበት አካባቢ እና ያልደረሰለት ህዝብም የለም ብለዋል።

ግሎባል አልያንስ ከዚህ ቀደም በመሰል ሁናቴ ለኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ከ15 ሚልዮን ብር የሚያወጡ የህከምና መርጃ መሳሪያዎችን፣በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝይድ ሆስፒታል የሳኒታይዘር ማምረቻ፣ለወልዲያ ጤና ተቋማትን መልሶ መገንባት ላይ ንቁ ተሳትፎዎችን ማድረጉ ይታወሳል።

61970cookie-checkከ265,000 ዶላር በላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE