ሴንቼሪ ፕሮሞሽንና ኢቨንትስ የገና በዓል ባዛርና ፌስቲቫል ማዘጋጀቱን አስታወቋል።

Reading Time: 2 minutes
የተለያዩ ባዛርና የንግድ ትርዒቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ሴንቼሪ ኘሮሞሽን እና ኢቨንት ፤ ከታህሳስ 6 ቀን እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ፤ ለ22ቀናት የሚቆይ «ገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል» በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ለማዘጋጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ሴንቼሪ ኘሮሞሽን እና ኢቨንት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤
ከገና የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል ባሻገር ድርጅቱ የተመሠረተበትን 25 የምስረታ በዓል በደመቀ መልኩ ከደንበኞቻቸው ጋር ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማነህ ገልጸዋል።

ከ500 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ትልቁ የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሉታቸውን ለተጠቃሚው የሚቀርብ ሲሆን በገና ባዛር ላይ የቤት ዕቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ የህፃናትና የአዋቂ አልባሳት ፣ የስጦታ ዕቃዎች የተለያዩ ምርቶች የሚሸጡ ሲሆን በተጨማሪም ለበዓል የሚሆኑ የአስቤዛ ምርቶች ለሽማቹ በአምራች ዋጋ ያለገደብ ይቀርባሉ።

ከዚህ ባሻገር በቀኑ በተወዳጅ ድምፃውያን በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል የሙዚቃ ዝግጅት የሚቀርብ ሲሆን
የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን ይህም ክፍያው የሚከናወነው በቴሌብር አማካኝነት እንደሆነም ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እና የገበያ ልማት ድርጅት ግቢ 25 ሚሊየን ብር ወጪ ወጥቶበት የማስፋፊያ ስራዎች እያደረገ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በአሁን ሰዓት በአዲስ መልክ በኮንከሪት አስፋልት ተሠርቷል። ለዚህ የማስፋፊያ ስራው ለገና የንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል ተሣታፊዎች አመቺ ሆኖ መታደሱ ብቻ ሣይሆን ተጨማሪ ተሣታፊዎችን ለማስተናገድ ምቹ እንደሚሆን ተገልጿል።

61950cookie-checkሴንቼሪ ፕሮሞሽንና ኢቨንትስ የገና በዓል ባዛርና ፌስቲቫል ማዘጋጀቱን አስታወቋል።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE