ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው ሕጋዊ ሰውነት በመያዝ ወደ ግንባታ የገቡ፣ የግንባታ ሥራ ጅማሮ ላይ ያሉ እንዲሁም በዝግጅት ደረጃ ላይ ያሉ ሳይቶችን የጉብኝት ፕሮግራም ተካሄደ!

Reading Time: 2 minutes
**
ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ‹‹ይዞታዬን አጋራለሁ! ከተማዬን አለማለሁ!›› በሚል መርህ ኅብረት ሥራ ማህበራት እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ኅዳር 08 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገው ጉብኝት ማህበራቱ እና ባለድርሻ አካላት በስፍራው ተገኝተው ማበረታቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ቃል ገብተዋል፡፡ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የመስክ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በዚሁ መሠረት በመጀመሪያ በጣሊያን ኤምባሲ አካባቢ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ወደ ሥራ የገባው የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማህበር በኅዳር 08 ቀን 2016 ዓ.ም ከሥራ ተቋራጭ ጋር በመፈራረም የቁፋሮ ሥራ የመንግሥት አጋር ድርጅቶች እና የኅብረት ሥራ ማህበሩ አባላት በተገኙበት ተጀምሯል፡፡

ኅዳር 09 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ ቡልጋሪያ ሳይት በክረምቱ ወር ግንባታ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የመስክ ምልከታ ተጋባዥ እንግዶች እና የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተደርጓል፡፡ የሾሪንግ ሥራ መጠናቀቁን እና ቁፋሮ በቅርብ ጊዜ በማጠናቀቅ እስትራክቸራል ማሳረፍ እንደሚጀመር የሥራ ተቋራጩ ለተገኙ እንግዶች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የኅብረት ሥራ ማህበሩ አመራር ግንባታው በቶሎ ለማጠናቀቅ ከሕንፃ ተቋራጩ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግንባታውን በታቀደበት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንዲቻል ለግነባታ የሚዋጣውን ቅድመ ክፍያ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

የላንቻ ሳይትን በሚመለከት ባለይዞታው ቦታውን በማፅዳት ለግንባታ ዝግጁ ያደረጉ ሲሆን የኅብረት ሥራ ማህበሩ ቀጣይ ተግባራት እንደተጠናቀቁ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን እንገልፃለን።

በአጠቃላይ በሦስቱም ሳይቶች የተደረገው ምልከታ ጥሩ መረጃ በሚባል እየተከናወነ መሆኑን እና በቀጣይ የኅብረት ሥራ ማህበሩ አባላት እና አጋር ተቋማት በቅንጅት በመሥራት ውጤታማ የሆነ ሥራ እንደሚጠበቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እስከአሁን በተከናወኑ ሥራዎች የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን አባላትን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡

61760cookie-checkጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ በመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው ሕጋዊ ሰውነት በመያዝ ወደ ግንባታ የገቡ፣ የግንባታ ሥራ ጅማሮ ላይ ያሉ እንዲሁም በዝግጅት ደረጃ ላይ ያሉ ሳይቶችን የጉብኝት ፕሮግራም ተካሄደ!

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE