የድል በር ትምህርት ቤት የስፖርት ማዘወተርያ ተመረቀ።

Reading Time: 2 minutes
ኤሴቅ ዲኮርና ኢቨንት ኦርጋናይዘር በድል በር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአንድ ሚሊዮን ብር ወጪ በማድርግ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የስፖርት ማዘወተርያ ሰርቶ ለትምህርት ቤቱ አበረከተ።

ድል በር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 07 ሰሜን ማዘጋጃ ከፍብሎ ሸገር መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ትምህርት ቤቱ በ1994 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን “ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ ተማሪዎች ፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።

በዛሬው መርሐግብር ኢትዮጵያ በማርሻል አርት ስፖርት ስሟን ከፍ አድርገው ያስጠሩ ስፖርተኞችን ፣ የመጀመሪያው የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ የስፖርት እና ሜዳ ስራ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች ኤሴቅ ዲኮርና ኢቨንት ኦርጋናይዘር እና ትምህርት ቤቱ የምስጋና ወረቀት እና የጋቢ ሽልማት አበርክተዋል።

የድል በር ትምህርት ቤት ምድረ ግቢ ለሰራተኞች ፣ ለመምህራን እና ለተማሪዎች ምቹ ከማድረግ ባሻገር የተማሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ ተጨማሪ የህንጻ ግንባታ ለማከናወን በዝግጅት ላይ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች እንዲሁም መላዊ ኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤቱ ለዚህ በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 10000114416127 ድጋፍ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

61700cookie-checkየድል በር ትምህርት ቤት የስፖርት ማዘወተርያ ተመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE