በዱከም ከተማ የተገነባው እና ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ራባ ሆቴል ዛሬ ህዳር 1 ቀን 2016ዓ.ም የኦሮሚያ ክልል እና የዱከም ከተማ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ፣ ከተለያየ አካባቢ የመጡ ባለሀብቶች፣ የአካባቢ ነዋሪዎች እንዲሁም ጢሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
ላለፉት ስምንት አመታት በግንባታ ላይ የነበረው ራባ ሆቴል 15 የመኝታ ክፍሎች ፣ ከ350 በላይ ሰዎችንም ማስተናገድ የሚችሉ ባህላዊ እና ዘመናዊ ሬስቶራንትን እንዲሁም ቪ አይ ፒ ባር የያዘ ሲሆን ከ28 በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሯል።
በአቶ መሰረት አምበዬ እና በባለቤታቸው ወይዘሮ ቆንጂት አብዲሳ የተገነባው ራባ ሆቴል በቅርቡ የማስፋፊያ ስራዎችን ሲያጠናቅቅ የምኝታ ክፍል ቁጥሩን ከፍ በማድረግ ስቲም ሳውና እንዲሁም ዋና ጨምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል በምረቃው መርሀግብር ላይ ተገልጿል።
ራባ ሆቴል የራሱ እርሻ ቦታ እንዳለው እና የራሱን ግብዓት ተጠቅሞ ንፁህ የምግብ አገልግሎት የሚያቀርብ ሲሆን
ዱከም ከተማ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ የኢንዱስትሪ ከተማ በመሆኗ እንዲሁም ለመዝናናት ተመራጭ ከሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በመሆኗ በርካታ ሰዎች ወደ ዱከም ከተማ ሲመጡ ለማረፊያ እና ለመዝናኛ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ሆቴል እንደሆነ ባለቤቶቹ ገልጸዋል።
የሆቴሉ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወይዘሮ ቆንጂት አብዲሳ ለሆቴሉ ግንባታ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
615100cookie-checkከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ራባ ሆቴል ተመረቀ።no