ድል በር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለቀድሞ ተማሪዎች ጥሪ አቀረበ።

Reading Time: 2 minutes
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በ1994 ዓ.ም የተመሠረተው ድል በር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተሠራውን የስፖርት ሜዳ የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም የቀድሞ ተማሪዎች ፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ትምህርት ቤቱ በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

የድል በር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ርዕሰ መምህር ከበደ ሶቦቃ “ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ ካሳለፍነው ክረምት ጀምሮ በትምህርት በቤቱ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸው የተሰሩ ስራዎችን የፊታችን ህዳር 1 ቀን 2016ዓ.ም ይመረቃሉ ብለዋል።

ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ስፍራ ከመሆናቸው ባሻገር የልጅነት እድሜያችንን ትዝታዎች የያዙ ጭምር በመሆናቸው ቀድሞ በድል በር ትምህርት ቤቱ ሲማሩ የነበሩ የያኔው ተማሪዎች አሁን ላይ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሠማርተው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የሚገኙ ተማሪዎች በመገኘት ትምህርት ቤቱን በሙያቸው እና በገንዘባቸው እንዲያግዙ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ከበደ ሶቦቃ ጥሪ አቅርበዋል ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ወጣቶች እና ስፖርት ኃላፊ ወጣት ፋሲል ብዙዓለም በበኩላቸው ኤሴቅ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በድልበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያካሄደ ያለው የሜዳ እድሳት ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑንን ገልጸው ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የድል በር ትምህርት ቤት ምድረ ግቢ ለሰራተኞች ፣ ለመምህራን እና ለተማሪዎች ምቹ ከማድረግ ባሻገር የተማሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ ተጨማሪ የህንጻ ግንባታ ለማከናወን በዝግጅት ላይ በመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎች እንዲሁም መላዊ ኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤቱ ለዚህ በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 10000114416127 ድጋፍ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

61310cookie-checkድል በር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለቀድሞ ተማሪዎች ጥሪ አቀረበ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE