ማህበሩ ለአረጋውያን የህክምና ማዕከል ለመገንባትና በአረጋውያን ሕክምና ዙርያ ሐኪሞች የሚሰለጥኑበትን ተቋም ለመመስረት አላማ ይዞ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሆነ በማህበሩ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ገብረስላሴ ለአራዳ ኤፍኤም ገልፀዋል::
የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር በዛሬ ዕለት 25ኛ ዓመት በዓሉን አስመልክቶም የተለያዩ መርሃ-ግብሮችን ማዘጋጀቱን አሳውቋል::
ከነገ በስትያ በብሔራዊ ሙዝየም የድርጅቱን የ25 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውድርዕይ ለእይታ ክፍት የሚያደርግ ሲሆን ህዳር 9/2016 ዓ.ም. ደግሞ የገቢ ማሰባሰቢያ ያከናውናል::
ማህበሩ እንጦጦ ኪዳነምህረት አካባቢ ለ18 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት አርባ አንድ ኢየሱስ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ እስከ 200 የሚደርሱ ዜጎችን እየረዳ ይገኛል::
@enqu(እንቁጣጣሽ ኃ/ማርያም )