በዓለም ዙርያ በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጥናቶች እና ቅኝቶችን በማድረግ የሚታወቀው ጋሉፕ የተሰኘው ተቋም ኩክፓድ ከተሰኘ የምግብ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመሆን ይፋ እንዳንደረገው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች በሳምንት በአማካይ ከአስር ጊዜ በላይ ምግብ የሚያበስሉ ሲሆን ወንዶች ግን ሁለት ጊዜ ብቻ ያበስላሉ ብሏል።
በወንዶች እና በሴቶች የምግብ ማብሰል ክንውኖች መካከል ያለው ልዩነትም በዓለም ላይ ጥናቱ ከተደረገባቸው አገራት መካከል ትልቁ ነው ተብሏል።
ከኢትዮጵያ በመቀጠል እስከ አስር ያለውን አገራት በብዛት የሰሜን አፍሪካ እና የመካከለኛው እስያ የተቆጣጠሩት ሲሆን ከመካከላቸውም ግብፅ፥ ኔፓል፥ የመን እና አልጀሪያ ይገኙበታል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን