ብዙ ያልተነገረለት ግዙፉ የሕፃናት መንደር ከተመሠረተ 37 አመትን አስቆጠረ

Reading Time: < 1 minute

ከዛሬ 37 ዓመት በፊት ማለትም በ1977 ዓ.ም በሀገራችን ኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው ከባድ ድርቅ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ለሞት እና ለስደት ዳርጓል።

በእዚህ ወቅት ማለትም ህጻናት ተርበው ተጠምተው ከሰውነት ጎዳና ወጥተው የሰው ያለህ ሲሉ የተመለከቱት ባላራዕይዋ እና ደጓ እናት ወ/ሮ ፀሐይ ሮሽሊ ባዩት ነገር ሁሉ ተረበሹ አይተው ማለፍ አልፈለጉም።

ህጻናትን ከሞት የመታደግ የኢትዮጵያዊነት ግዴታቸውን ለመወጣት በቻሉት ሀቅም ህጻናትን መርዳትና ማገዙን ጀመሩ በ1978 ዓ/ም ሰላም የህጻናት መንደርን መሠረቱ።

ይህ የህጻናት መንደር በርካቶችን አሳድጎ ትልቅ ደረጃ አድርሷል ለብዙዎችም የህይወት መቀናት መንገድን አመቻችቷል።

በአሁን ሰአትም “መስጠት መታደል ነው” በሚል መሪ ቃል ብዙ ህጻናትን እየረዳና እያገዘ የሚገኘው ሰላም የሕጻናት መንደር በዛሬዉ ዕለት በዲጂታል ማርኬቲግንግ የሀብት ማሰባሰብ ስራውን ወሰን ሂል ሳይድ ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው በግዙፉ ግቢው በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንግዶች ፣የቦርድ አመራሮች እና አርቲስቶች በተገኙበት በይፍ አስጀመሯል።

የሰላም የሕጻናት መንደር ኢክስኪዮቲቪ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ጫሊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ስላም የሕጻናት መንደር ላለፋት 37 ዓመታት የተለያዩ የልማት ስራዎች ሲያከናን የቆየ መሆኑን ጠቅሰዉ የልማት ስራዉ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን የተለያዩ የሀብት ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በመቀየስ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸው ሀብት ለማሰባሰብ ከታቀዱ ዘዴዎች መካከል የዲጂታል ማርኬቲንግ አንዱ መሆኑንና ስራውንም ባሳለፍነው ሳምንት በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

እንዲሁም የስላም የሕጻናት መንደር የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ወንድወሰን ተሾመ ግለሰቦች፣ ባለሃብቶች፣ የመንግስትና የግል ድርጅቶች፣ ካምፓኒዎች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ሌሎችም በሚችሉት አቅም የቻሉትን ሁሉ በመለገስ ስላም የጀመራቸዉን የበጎ አድራጎትና የልማት ስራዎች በማገዝ የበርካቶችን ህይወት መታደግ እንዲቻል ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።

የእዚህ ግዙፍ የህጻናት መንደር መሥራች ልበ ቀናዋ እና ደጓ እናት ወይዘሮ ጸሀይ ይህን መንደር ስመሠርተው ብቻዬን አይደለም የመሠረትኩት ዘር ቀለም፣ ሀይማኖት ጾታ ያልመረጠ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከጎኔ ነበረ አሁንም ብዙ ኢትዮጵያውያን ከጎናችን ስለሆነ እናመሠግናለን።

በሲውዘርላንድ እና በተለያዩ አለማት የምትገኙ የሠላም የህጻናት መንደር ደጋፊዎችና ቤተሰቦች እናንተንም ከልብ እናመሠግናለን።

ለእዚች ወርቅ እና ብርቅ ለሆነች ለውቧ ኢትዮጵያ ሰላምን ፍቅርን አንድነትን ይስጥልን። በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
61250cookie-checkብዙ ያልተነገረለት ግዙፉ የሕፃናት መንደር ከተመሠረተ 37 አመትን አስቆጠረ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE