3ኢ ኤቨንትስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መሃንዲሶች ማህበር ጋር በመተባበር 4ተኛውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ኤግዚቢሽን ” ኃይል ቁጠባ ለምለም አፍሪካ ” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያካሂድ ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2016ዓ.ም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀ።
በዚህ ኤግዚቢሽን በኤሌከትሪክ፣ ኤሌክትሪሲቲ፣ የመገናኛ ብዙሃን ቴከኖሎጂ፣ አዉቶማቲክ የግንባታ፣ የደህንነት፣ ቴሌኮሚኒኬሽን፣ የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪከ እና ሌሎችም በኤሌክትሪሲቲ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ከአገር ዉስጥና ከአገር ውጭ ያሉ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ ሻጮች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ሲሆን ምርት እና አገልግሎታቸውን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።
3ኢ ኤቨንትስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መሃንዲሶች ማህበር በቅንጅት በሚያዘጋጁት ኤግዚቢሽን ላይ ከ 300 በላይ የሚሆኑ በሃገር ውስጥ ያሉና ከውጭ የሚመጡ በኤሌክትሪሲቲ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾች፣ አስመጪዎችና አቅራቢዎች እና ከመቶሺህ በላይ የሚሆኑ ጎብኚዎች የሚሳተፉበት ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ሲምፖዚየሞች፤ ሴሚናሮች የሚካሄዱበት እና ጥናታዊ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እንደሆነ የ3ኢ ኤቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱል ፈታ አሊ ገልጸዋል።
25ኛ አመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መሃንዲሶች ማህበር ኘሬዝዳንት ኢንጂነር አማረ አሰፋ በመግለጫው እንደገለጹት በዘርፉ የተሠማሩ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ የሚያሳዩበት ከመሆኑ ባሻገር የሀገር በቀል ድርጅቶችን የወጪ ገቢ ንግድ ስርዓት የሚበረታታበት ፤ የመረጃ ትስስሮን ማጎልበት፣ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን መለዋወጥ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል።
አዘጋጆቹ በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት ተቋማት በኤግዚቢሽኑ ላይ ተሳታፊ ከመሆን በተጨማሪ ዝግጅቱን አጋር እንዲሆኑ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
611600cookie-checkየኢትዮጵያ ኤሌክትሪሲቲ ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው።no