ከወርሃ መስከረም 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ሲከበር የነበረው የዓለም የቱሪዝም ሳምንት በዓለም ለ44ኛ በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ ”ቱሪዝም ለአረንጓዴ ልማት – አረንጓዴ ልማት ለቱሪዝም!” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ ለመከበር በታላቅ ድምቀት በይፋ ተከፈተ፡፡
በክብረ በዓሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ ቡዜና አብዱልቃድር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ፣ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ በከተማችን ያሉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ከሁለት ሚሊየን በላይ የከተማችን ነዋሪዎች ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ክብረ በዓሉ ከዛሬ ጥቅምት 20/2016 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የንግድና ስራ እድል ፈጠራ ትርዒት፣ የሚስ ቱሪዝም አዲስ አበባ 2016 ውድድር፣ የሁለተኛ ዙር የበጎ አድራጎት የደም ልገሳ፣ የጥያቄና መልስ ውድድር፣ የዕውቅናና ሽልማት ስነ-ሥርዓት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን