«በጥቅምት አንድ አጥንት» የስጋ ፌስቲቫል በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።

Reading Time: < 1 minute
ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ከቢጂአይ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር «በጥቅምት አንድ አጥንት» የስጋ ፌስቲቫል ለ8ኛ ጊዜ አዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለስምንተኛ ጊዜ ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ተከፈተ።

ሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ፌስቲቫል ላይ አንድ ኪሎ ስጋ በ800 ብር እየተሸጠ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ዘጠኝ ስጋ ቤቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የኘሮግራሙ አዘጋጅ ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘውግ ጀማነህ ለየኔ ቫይብ ዝግጅት ክፍል እንደገለጹት ላለፉት ስምንት አመታት የኘሮግራሙ ዋና አጋር ለሆነው ለቢጂአይ ኢትዮጵያ ምስጋናቸውን አቅርበው የስጋ ፌስቲቫል ከጥቅምት ወር ባሻገር በአመት ሁለቴ ለማዘጋጀት በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሴንቸሪ ኘሮሞሽንና ኤቨንትስ በ 1991 ዓ.ም የተቋቋመ የማስታወቂያና የፕሮሞሽን ድርጅት ሲሆን ተቋሙ በያዝነው ዓመት የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን በልዮ ድምቀት የሚያከብር ሲሆን መጪውን የገና እና የፋሲካ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ጨረታ ማሸነፉ ይታወሳል።

60830cookie-check«በጥቅምት አንድ አጥንት» የስጋ ፌስቲቫል በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE