ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ «ይግዙ ፣ ይሽጡ ፣ ይሸለሙ » በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ቀጥተኛ የንግድ ደንበኞቹን ለማበረታታትና ላለፉት ሶስት ወራት እያካሄደ ከሚገኘው የዕጣ ሽልማት ውድድር ከ25,000 ተሳታፊዎች ውስጥ የመጀመርያ ዙር 70 አሸናፊዎቻችን ትናንት ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር 70 የፍሪጅ ዕጣ በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ አውጥቷል።

ኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በተሰጠው ፈቃድ መሰረት ካለፈው ነሃሴ 29 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ የሎተሪ ፕሮሞሽን በአዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ ቀጥተኛ የንግድ ደንበኞቹ እያካሄደ መሆኑን የኮካ ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ማናጀር ወይዘሮ አብነት ጸጋዬ በመርሐግብሩ ላይ ለተገኙ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ወራቶች ውስጥ በአዲስ አበባ የሱቅ ባለቤት፣ አከፋፋይ ወይም የሬስቶራንት ባለቤት ለሆኑ የድርጅቱ ደንበኞች 5 ሳጥን ወይም እሽግ የኮካ ኮላ ወይም 3 ሳጥን እና 3 እሽግ ፋንታ ኦሬንጅ ምርቶችን ከኮካ-ኮላ አከፋፋይ ሲያወርዱ ነፃ ምርት እንዲሁም ከ200 በላይ ፍሪጆችን ለሽልማት ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

ኮካኮላ ከዚህ ቀደም የሽልማት እጣ የሚያከናውነው ለደንበኛች ሲሆን አሁን ላይ የንግድ ቤቶች ያለባቸውን የተለያዩ ችግሮች በመመልከት ይህን የፍሪጅ የሽልማት እጣ እንደጀመረ የተገለፀ ሲሆን እጣው የደረሳቸው ደንበኞች ፍሪጆቹን ለፈለጉት ዓለማ እንዲጠቀሙበት
ሙሉ በሙሉ የባለቤትነት መብት እንደሚሰጣቸው
የኮካኮላ ማርኬቲንግ ማናጀር ወይዘሮ አብነት ጸጋዬ ተናግረዋል።

በተጨማሪም 2ኛ ዙር የሽልማት እጣ ከ1 ወር በኃላ እንደሚወጣ የተገለፀ ሲሆን በትናንትናው እለት እጣ የወጣላቸው ባለእድለኞች በኮካ ኮላ የቴሌግራም ፣ የፌስቡክና የኢንስታግራም ድረ ገፆች ላይ አሸናፊዎችን መመልከት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
608100cookie-checkኮካኮላ የንግድ ቤቶቹን ለማበረታታት ለባለዕድለኞች የፍሪጅ የሽልማት እጣ አካሄደno