ኢትዮ ጋይድ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ተዋወቀ።

Reading Time: 2 minutes
መኖሪያቸውን በሀገረ አሜሪካ ሀገር ያደረጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሁለት አመት በፊት ዚ ትራክ የተሰኘ መተግበሪያ በጭነት ትራንስፖርት (ሎጂስቲክ) ላይ የተሰማሩ አስተላላፊዎች ፣አሽከርካሪዎችና ደንበኞች በቀላሉ በግልጽ የሚግባቡበትን መተግበሪያ በመስራት አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል።

የዚትራክ እህት ኩባንያ የሞባይል መተግበሪያ አፕሊኬሽን የሆነውን ኢትዮ ጋይድ የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ በመፍጠር ለተጠቃሚው ዘመናዊና የተቀላጠፈ አሰራር ይዞ ቀርቧል።

ኢትዮጋይድ የሞባይል መተግበሪያ ተጠቃሚዎች የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን(መደብሮችን)፤ አገልግሎቶችን
እና የተለያየ የሙያ ዘርፍ ነጋዱዎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ ተሠርቷል።

እንደሚታወቀው በቀደመው ጊዜ የንግድ ድርጅች ባለቤቶች መደብሮቻቸውን በቢጫው መዝገብ(Ye||ow Page) እንዲመዘገብ በማድረግ ለተጠቃሚዎች እድራሻቸውን ፣ የስልክ ቁጥራቸውን፣ የቅርንጫፋቸውን ብዛት እና መሰል መረጃዎችን በቀላሉ እንዲገኙ ያደርጉ ነበር፡፡ ኢትዮ ጋይድ መተግበሪያ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የቢጫውን መዝገብ አገልግሎት እጅግ ዘመናዊ እና ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት እንዲሆን እጅግ ከፍ ተደርጎ የተሠራ የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡

የንግድ ድርጅቶች በቀላሉ እንዲተዋወቁ ብሎም ተጠቃሚዎች በአቅራቢያቸው ያሉትን ጠቃሚ መደብሮች በስልካቸው ላይ በማሳየት እና ከመደብሮቹ ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ መሆኑን የቴክኖሎጂው መስራች እና ባለቤት አቶ ኃይለእየሱስ ዘሪሁን የሞባይልጰመተግበሪያውን ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ባስተዋወቁበት መድረክ ላይ ገልጸዋል ።

ኢትዮጋይድ የሞባይል መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በቀላሉ የሚፈልጉት የንግድ ድርጅት መረጃ ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ መሠራቱን በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን የሚፈለገው የንግድ ድርጅት(መደብር) የት እንደሚገኝ ፤ ምን አገልግሎት እንደሚሰጥ ፣ መደብሩን ማነጋገር ቢፈለግ በቀላሉ መደወል፤ ቦታውን በመጠቆም ወይም መልዕክት መላክ እንዲቻል ተደርጎ መሰራቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጋይድ የሞባይል መተግበሪያ ለሁሉም ስልኮች እንዲያገለግል በማሰብ በፕለይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ላይ መተግበሪያውን በማውረድ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።
https://ethioguide.net

60550cookie-checkኢትዮ ጋይድ የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ ተዋወቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE