ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ በምስራቅ አፍሪካ በግዙፉነቱ የሚጠቀስ በኢትዮጵያ ደግሞ የመጀመሪያ የሆነ በአንድ ጊዜ ከአንድ ሺህ በላይ ሰው የሚይዝ የዳንስ ፊትነስ ስቱዲዮ ፣ የተሟላ ጂምናዚየም እና ስፓ በመገንባት ከዳንስ ፊትነስ በተጨማሪ በተሟላ መሳሪያ እና በፕሮፌሽናል አሰልጣኞች በመታገዝ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ለማብሰር ጥቅምት 9 እና ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ እንደሚመረቅ የኢትዮ ዳንስ ፊትነስ መስራች እና ባለቤት ቶማስ ኃይሉ (ቶም ኘላስ) ዛሬ በማዕከሉ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቀ።
ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ከ850 በላይ ቋሚ አባላት እና በየዕለቱ እስከ 100 የሚደርሱ ደንበኞችን ያፈራ የስፖርት ማዕከል ሲሆን የፊታችን ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ከ10ሺ በላይ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት “ወደ ህልማችን”በሚል መሪ ቃል ታላቅ የፊትነስ ዳንስ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ በዛሬው መግለጫ ተገልጾአል።
ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከናወነው የምረቃ ኮንሰርት ከ500 እስከ 2000 ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን
በዚህ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ውስን ሰዎች ትኬት ገዝተው እንዲገቡ የተመቻቸ ሲሆን የመግቢያ ዋጋው 500 ብር መሆኑን ተገልጿል።
ቶማስ ኃይሉ (ቶሚ ፕላስ) የኢትዮዳንስ ፊትነስ መስራች እና አሰልጣኝ ሲሆን ይህንን ስፖርት ከመጀመሩ አስቀድሞ ከ40 በላይ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በተወዛዋዥነት በኬሮግራፈርነት ሰርቷል።
ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ይህንን ዓለም አቀፍ ልምድ ወደ ሃገር ውስጥ በማምጣት ሀገራዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ የመጣ ስልት ሲሆን ላለፉት አራት ዓመታት በዮሊ የፈትነስ ማዕከል ውስጥ ልምምድ ሲሰጥ ቆይቶ አሁን ደግሞ ራሱ ባስገነባው ዳንስ ፊትነስ ስቱዲዮ፣ ጂምናዚየም እና ስፓ በስፋት መስጠት ከጀመረ ሶስት ወራት ተቆጥሯል።
605200cookie-checkአዲሱ ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጂም እና ስፓ ሊመረቅ ነው።no
ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ከ850 በላይ ቋሚ አባላት እና በየዕለቱ እስከ 100 የሚደርሱ ደንበኞችን ያፈራ የስፖርት ማዕከል ሲሆን የፊታችን ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ከ10ሺ በላይ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት “ወደ ህልማችን”በሚል መሪ ቃል ታላቅ የፊትነስ ዳንስ ኮንሰርት እንደተዘጋጀ በዛሬው መግለጫ ተገልጾአል።
ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከናወነው የምረቃ ኮንሰርት ከ500 እስከ 2000 ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን
በዚህ ዝግጅት ላይ ለመሳተፍ ውስን ሰዎች ትኬት ገዝተው እንዲገቡ የተመቻቸ ሲሆን የመግቢያ ዋጋው 500 ብር መሆኑን ተገልጿል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
ቶማስ ኃይሉ (ቶሚ ፕላስ) የኢትዮዳንስ ፊትነስ መስራች እና አሰልጣኝ ሲሆን ይህንን ስፖርት ከመጀመሩ አስቀድሞ ከ40 በላይ የሙዚቃ ቪዲዮዎችን በተወዛዋዥነት በኬሮግራፈርነት ሰርቷል።
ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ይህንን ዓለም አቀፍ ልምድ ወደ ሃገር ውስጥ በማምጣት ሀገራዊ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ የመጣ ስልት ሲሆን ላለፉት አራት ዓመታት በዮሊ የፈትነስ ማዕከል ውስጥ ልምምድ ሲሰጥ ቆይቶ አሁን ደግሞ ራሱ ባስገነባው ዳንስ ፊትነስ ስቱዲዮ፣ ጂምናዚየም እና ስፓ በስፋት መስጠት ከጀመረ ሶስት ወራት ተቆጥሯል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ