በለንደን በሚካሄደውን የ2023 አራተኛው አመታዊ የኢትዮጵያ ፊልም በዓልን አስመልክቶ በሀያት ሪጀንሲ የቅድመ መክፈቻ ሥነ ስርዓት ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም አመሻሽ ላይ “ሐበሻ ቪው” የማስተዋወቅና ዕውቅና የመስጠት ዝግጅት አካሂዷል።
ባህሎቻችንን እና የዘመኑን እይታ የያዙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎችን ጥበብ እና ፈጠራ በተለያዩ የዓለም መድረክ ሲያሳይ መቆየቱን “የሐበሻ ቪው” ስራ አስፈፃሚና መሥራች ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ የኢትዮጵያ ፊልም ዝግጅት በለንደን ተካሂዶ የነበር ሲሆን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፊልም “ኂሩት አባቷ ማነው?” እና “ሲመት” ለተመልካቾች ቀርበውም እንደነበር። ገልጸው ዘንድሮም የተመረጡት “ፀፀት” እና “ዝምታዬ” የተሰኙ ሁለት የኢትዮጵያ ፊልሞች ሲሆኑ ጥቅምት 17 እና 18 2016 ዓ.ም በታዋቂው የለንደኑ “ሪትዚይ ሲኒማ” ለእይታ ይበቃሉ ብለዋል።
በውጪ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ ሥነጥበብ፣ ኪነጥበብ ፣ ክውን ጥበባት ጋር የሚያገናኙ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም “ሐበሻ ቪው” ኢንተርኔትን ብቻ በመጠቀም በእጅ ስልክ፣ ታብሌት ወይም በኮምፒውተር አማካይነት ለተለያዩ የእድሜ ክልል የሚሆኑ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች፣ ከ50 በላይ የዜና፣ ሙዚቃ፣ ስፖርት እና በርካታ የመዝናኛ አማራጮች ያሉት እንዲሁም ዓለም አቀፍ የቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉበት መተግበሪያ ያለው ድርጅት ነው ተብሏል።
በምሽቱ ዝግጅት ከቀደምት ከያኒያን መሀከል የብዙዎች የኪነ- ጥበብ አባት ተብሎ የሚጠራው ተስፋዬ ሲማ የቀድሞ ፊልሞችን ለመስራት ምን ያህል አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደነበሩ ጠቅሶ ፊልሞቻችን በአለም ዓቀፍ መድረክ ለዕይታ መብቃታቸው የሀገራችንን ፊልም የሚያበረታታና አንድ ዕርምጃ እንዲያድግ ያደርገዋል ብሏል።
600500cookie-checkየኢትዮጵያ ፊልሞች በቀጣይ ሳምንት በለንደን ከተማ መድረክ ሊቀረቡ ነው!no