በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው ፤ ሩሁም የሩማቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ተመረቀ።

Reading Time: < 1 minute
«ጥራት እና ክብካቤ የተሞላበት ህክምና ! » በሚል መርህ
ሩሁም የሩማቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በአገራችን ያለውን የመገጣጠሚያ፣አያያዥ ጡንቻዎች አና ችግሮች ህክምና ክፍተት ለመሙላት ሳይንሳዊ መሰረት ያለው የህክምና ተቋም አዲስ አበባ ጨርቆስ ታቦት ማደሪያ አጠገብ በከፈተው ልዮ ክሊኒክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ሩሁም የሩማቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ በአገራችን ያለውን የመገጣጠሚያ፣ አያያዥ ጡንቻዎች እና ችግሮች ሕክምና ክፍተት የመሙላትን አላማ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን የክሊኒኩ መስራች ዶ/ር ብርሀኑ ደመላሽ በምረቃው መርሐግብሩ ላይ የገለጹ ሲሆን ክሊኒኩ በተለይም በጤና ዘርፉ ላይ የሚታየዉን ሥራ አጥነት እና የልዩ ሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት ውስንነት ለመፍታት እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ ከ20 በላይ ለሚሆኑ ቋሚና የትርፍ ሰዓት ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።

በክኒሊኩ ሥራ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊ ዶ/ር ኢሉባቦር ቡኖ፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነ መስቀል ጠና፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሲሳይ ስርጉ፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል።

60030cookie-checkበኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው ፤ ሩሁም የሩማቶሎጂ እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ተመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE